የጀርመን እና የኢትዮጵያ የልማት እርዳታ ስምምነት  | ኢትዮጵያ | DW | 03.11.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የጀርመን እና የኢትዮጵያ የልማት እርዳታ ስምምነት 

«የጀርመን መንግሥት እርዳታ በዋናነት ለትምሕርት ጥራት ለተግባረ ዕድ ትምሕርት እንዲሁም ለተፈጥሮ ጥበቃየሚውል ነው» የኢትዮጵያ የገንዘብ እና የኤኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴታ አቶ አድማሱ ነበበ ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:39
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:39 ደቂቃ

እርዳታው በዋናነት ለትምሕርት ጥራት ለተግባረ ዕድ ትምሕርት እንዲሁም ለተፈጥሮ ጥበቃ ይውላል

የጀርመን እና የኢትዮጵያ መንግሥት ፣ በኢትዮጵያ ለተለያዩ የልማት ዘርፎች እርዳታ የሚውል የአንድ ቢሊዮን ሁለት መቶ ሚሊዮን ዩሮ የእርዳታ ስምምነት ሰነድ ዛሬ ተፈራረሙ። ለ3 ዓመታት የሚዘልቀው ይህ የጀርመን መንግሥት እርዳታ በዋናነት ለትምሕርት ጥራት ለተግባረ ዕድ ትምሕርት እንዲሁም ለተፈጥሮ ጥበቃ እንደሚውል ከኢትዮጵያ በኩል ስምምነቱን የፈረሙት የገንዘብ እና የኤኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴታ አቶ አድማሱ ነበበ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። በጀርመን የልማት እና የኤኮኖሚ ተራድኦ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ከሰሀራ በስተደቡብ ያሉ የአፍሪቃ ሃገራት ክፍል ኃላፊ ዶክተር ሽቴፋን ኦስቫልድ የእርዳታው ዓላማ የሰለጠነ የሰው ኃይል ማፍራት እና ጠንካራ ኢትዮጵያን ማየት መሆኑን ለዶቼ ቬለ አስረድተዋል። በፊርማው ስነ ስርዓት ላይ የተገኘው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል። 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic