የጀርመን እና አሜሪካ የስለላ ዉዝግብ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 07.07.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመን እና አሜሪካ የስለላ ዉዝግብ

ጀርመን አንድ ዜጋዋ በሀገሪቱ የስለላ ተቋም ተቀጥሮ ለዩናይትድ ስቴትስ እንደሚሰልል ከደረሰችበት ወዲህ ጉዳዩ የሀገሪቱን ከፍተኛ የፖለቲካ ኃይሎች እያነጋገረ ነዉ። በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለመሰላለልን ስምምነት ለመፈረም ዝግጁ አለመሆኗን ዋሽንግተን ባለፈዉ ሳምንት መገባደጃ ላይ አመልክታለች።

የአሜሪካን የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ቤን ሮደስ ለዘጋቢዎች በጉዳዩ ላይ ባደረጉት ገለፃ ሀገራቸዉ ከየትኛዉም ሀገር ጋ እንዲህ ዓይነት ዉል የላትም ነዉ ያሉት። እንዲህ ያለ አለመግባባትን የሚያስከትል ሁኔታ ሲከሰትም በመነጋገር መፍትሄ እስኪያገኝ ጊዜ እንደሚወስድም ከማመልከት ሌላ መረጃ እንዳቀበለ ስለተደረሰበት ጀርመናዊ ጉዳይ የተባለ ነገር የለም። ግለሰቡ 218 ዶሴዎችን ለዩናይትድ ስቴትስ በ25 ሺ ዩሮ መሸጡን ማመኑ የተገለጸ ሲሆን ቀጣይ ምርመራዎችም እንደሚኖሩ ነዉ የጀርመን የሀገር ዉስጥ ሚኒስትር ቶማስ ዴሜዚር የገለፁት። መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የተባለዉ እዉነት ከሆነ ከባድ ጉዳይ ነዉ ማለታቸዉ ተዘግቧል። ይህን አስመልክቶ የጀርመን መገናኛ ብዙሃን የሚሉትን አካቶ እንዲያስረዳን የበርሊኑን ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለሚካኤልን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic