የጀርመን እርዳታ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ስደተኞች | ኢትዮጵያ | DW | 16.08.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጀርመን እርዳታ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ስደተኞች

የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ለተጠለሉ ስደተኞች የምግብ እርዳታ የሚውል 4.3 ሚሊዮን ዶላር ከጀርመን መንግሥት ሰሞኑን ተቀበለ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:09

የጀርመን የገንዘብ ድጋፍ

የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገንዘቡ በኢትዮጵያ ለሚገኙ 600,000 ስደተኞች የምግብ ወጪ እና የገንዘብ ድጎማ የሚውል መሆኑን አስታውቋል። ስደተኞቹ ከኤርትራ፤ ደቡብ ሱዳን፤ ሱዳን እና ሶማሊያ የመጡ መሆናቸውንም ገልጧል። የጀርመኑ አምባሳደር ዮዓኺም ሽሚት ለስደተኞች ጉዳይ ጀርመን ከፍተኛ ፖለቲካዊ ትኩረት እንደምትሰጥ ጠቁመዋል። የዓለም የምግብ ድርጅት የኢትዮጵያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጆን አይሌፍ ጀርመን ያደረገችው የገንዘብ ድጋፍ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

እሸቴ በቀለ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic