የጀርመን ኢንዱስትሪ ኩባንያዎችና አፍሪቃ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 21.05.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመን ኢንዱስትሪ ኩባንያዎችና አፍሪቃ

በአፍሪቃው ክፍለ ዓለም ፤ በዛ ያሉ አካባቢዎችና ሃገራት የዕድገት እመርታ በማሳየት ላይ መሆናቸው እየተነገረላቸው ነው። ከዚህ ቀደም የጀርመን አነስተኛና መለስተኛ ኢንዱስትሪ ኩባንያዎች፤ አፍሪቃ ውስጥ ሥር የሰደደ ሆኗል በሚባለው

 ሙስና፤ አስተማማኝ ያልሆነ የህግ ዋስትና  እንዲሁም የወንጀል መስፋፋት ሳቢያ ወደተጠቀሰው ክፍለ ዓለም፤  ፊታቸውን ከማዞር ቆጠብ ማለትን ይመርጡ ነበር። ይሁንና ክፍለ-ዓለሙ፤ ሌሎችን የሚያማልልበት ሁኔታ ባለመታጣቱ የጀርመን መካከለኛ እንዱስትሪዎች፤ ማሰላሰላቸው አልቀረም ። እንዲያውም፤ አውሮፓ ውስጥ ፣ የኤኮኖሚው ዕድገት በመንፏቀቅ ላይ ሳለ በአንዳንዶቹም ሃገራት ባለበት በቆመበት ወቅት፤ አፍሪቃ ውስጥ አንዳንድ አገሮች፤ ከ 10 ከመቶ በላይ ዕድገት ማስመዝመገባቸው ይነገርላቸዋል። በአጠቃላይ ፣ ክፍለ ዓለሙ፤ እንደ ዓለም ባንክ ትንበያ፣ ከ 5 ከመቶ በላይ ይሆናል ዕድገት የሚያስመዘግበው። በዚህ ላይ ፤ አንዳንዶቹ የአፍሪቃ አገሮች በተፈጥሮ ሀብት፤ በማዕድንና በመሳሰለው የከበሩ መሆናቸውም ሊዘነጋ አይገባም።

አፍሪቃውያን ፤ ከዐበይት ችግሮቻቸው አንዱ መሠረተ-ልማት ነው፤ 80 ከመቶው ህዝብ የኤልክትሪክ አገልግሎት የተነፈገው ነው። ከ 40 ከመቶ በላይ የሚሆነው ህዝብም፤ ንፁህ የሚጠጣ ውህ አቅርቦት አያገኝም። የመገናኛውና የመጓጓዣው ይዞታ ደግሞ ገና እጅግ ብዙ ይቀረዋል። የ Pecher ኢንጂኔር ቢሮ በሚሰኝ ድርጅት ፣ የውሃና ፍሳሽ እንዲሁም የመሠረተ-ልማት ፕሮጀክቶች ጉዳይ አማካሪ ሆነው የሚሠሩት  ሴኔጋላዊው አቡበከር ሴክ ፤ «እጅግ ብዙ ጉድለት አለ፣ ጉድለት ባለበት ቦታ ደግሞ ያን ለማሟላት ብዙ ጥያቄ ይኖራል» ይላሉ።  Trans Africa Invest የተባለው ምክር ሰጪ ኩባንያ ባልደረባ ሃርትሙት ዚፐር እንደሚሉት ፣ አንዱ ዐቢይ ጉደለት የሥራ ማንቀሳቀሻ ወረት ነው።   ታዲያ በተጠቀሰው ተፈላጊ ጉዳይ በማትኮር ፤ አንዳንድ ፣ ወረት ይዘው በመግባት በተገቢ ቦታ የሚያውሉ ወገኖች ትርፍ ማግኘታቸው የማይቀር ነው ሲሉ ያስረዳሉ።   እርግጥ  በአፍሪቃ ሥራ ላይ የሚውለውና ተመልሶ የሚገኘው ወረት መጠን ፤ እዚህም ላይ የወለድ ጉዳይ አስተማማኝነት ላይኖረው ይችላል፣ የሚሉት ደግሞ የአንድ የግንባታ ጉዳይ ኩባንያ ባልደረባ የሆኑት Heinz Rittmann የተባሉት ናቸው። እርግጥ ነው አፍሪቃ ውስጥ ፣ማሺኖችና የተለያዩ የግንባታ መሥሪያዎች ፣ ዋጋቸው ፣ ከአውሮፓ ይልቅ እጅግ ይወደዳል። ይሁን እንጂ ለሠራተኞች የሚከፈለው ደመወዝ ፣ እጅግ አነስተኛ በመሆኑ፣ኢንዱስትሪ ኩባንያዎቹ፤ ለመወዳደር እንዲሠማሩ እንጂ እንዲተውት አይደለም  የሚገፋፋቸው።

በመሠረቱ፤ገንዘብን ሥራላይ ለማዋል የሚሠራውና የሚሠራበት ደንብ የታወቀ መሆን አለበት ፤ ይህን ጠንቅቀው ካወቁም በኃላ ነው ፣ወደ  ጨረታ መግባቱ የተሻለ የሚሆነው። በአውሮፓውያን እዚህም ላይ በጀርመናውያን ኢንዱስትሪ ኩባንያዎች ዘንድ አፍሪቃ በአዎንታዊ መልኩ ስለማይታይ ሃይንትዝ ሪትማን፣ በመጀመሪያ ፤ ይህን አሉታዊ ስዕል ማስወገድና  ገሐዳዊን ይዞታ በሚገባ ማጤን ይበጃል ይላሉ።

ሰፊ ወረትን መልሶ መተካት መቻሉን፤ ገንዘብ ሥራ ላይ የሚውልበት ሀገርም ሰፊ የተፈጥሮ ሃብት  ያለው መሆኑን የሚያገናዝቡ የጨረታ ተወዳዳሪዎች አልታጡም።   ለምሳሌ ያህል የቻይና ኩባንያዎች፤ ያላብዙ ውጣ ውረድ፤ከቻይና ባንክ ዋስትና ይሰጣቸዋል። በጀርመን ግን፣  ሪትማን እንደሚሉት  ተመሳሳይ ዋስትና ለማግኘት ፣ ማመልከቻው ምላሽ እስኪያገኝ እጅግ ረዘም ያለ ጊዜ ነው የሚወስደው።

ያም ሆኖ የጀርመን ኢንዱስትሪ ኩባንያዎች ፤ አማራጭ ሐሳቦችን በመሠንዘር ፤ የመሣሪያና የሥራ ጥራትንም በማሳየት ይበልጥ የሚመረጡበት ዕድል አያታጣም።

ቻይናውያን ጨረታው ሲሰጣቸው ፣ አብዛኛውን ጊዜ ሁሉንም ከሀገራቸው ነው የሚያስመጡት። ወረት፤ ሠራተኞችእንዲሁም ማሺኖች!በዚህ ዓይነት አሠራር ደግሞ የአገር ውስጥ ኩባንያዎች አያተርፉም። የአገሬው ተወላጆችም የሥራ ዕድል አያገኙም።  አቡበከር ሴክ እንደሚሉት፤ አውሮፓውያኑ፤ የመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸው አፍሪቃውያን አኀዝ  ከፍ እንዲል ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። አፍሪቃውያን ፤ ውድና ጥሩ ዕቃ ከአውሮፓ በተለይ ከጀርመን መግዛት እንዲችሉ ማብቃት ሁሉንም ይጠቅማል። እስካሁን አፍሪቃ ብዙ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ገዝተው ከሚጠቀሙት ተራ የሚመደብ አይደለም።  ይሁን እንጂ የመካከለኛ ገቢ የሚያገኘው ክፍል ቁጥር እየጨመረ ነው። በግምት 60 ሚሊዮኑ የሚሆኑ የአፍሪቃ ተወላጆች የዓመት የነፍስ-ወከፍ ገቢያቸው፣ 3,000 የአሜሪካ ዶላር ነው። በጀርመን የኤኮኖሚ ሚንስቴር ፤ የውጭ ኤኮኖሚ ጉዳይ ተጠሪ ድርጅት የሆነው፤ (German Trade & Invest) የጀርመን ንግድና ውዒሎተ ንዋይ፣  እንደሚለው፤ ባለመካከለኛ  ገቢዎቹ  አፍሪቃውያን ፤ በ 3 ዓመት ውስጥ ቁጥራቸው ወደ 100 ሚሊዮን ክፍ ማለቱ አይቀርም።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

WWW links

 • ቀን 21.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14zKH
 • ቀን 21.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14zKH