የጀርመን ተቀናቃኝ ፓርቲ መሪዎች ክርክር | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 18.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመን ተቀናቃኝ ፓርቲ መሪዎች ክርክር

ለመራሔ-መንግሥትነቱ የሚወዳደሩት የሁለቱ ትላልቅ የፖለቲካ ማሕበራት እጩዎች ዛሬ የምርጫ ዘመቻ ፉክክር የመሠለ የፊት ለፊት ክርክር አድገዋል።በሥልጣን ላይ ያሉት መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል የዩሮን ኪሳራ ለማቃለል ተጣማሪ መንግሥታቸዉ የወሰደዉ እርምጃ ጥሩ ዉጤት አምጥቷል ባይ ናቸዉ

Bildcombo: Berlin/ Bundeskanzlerin Angela Merkel (CDU) gestikuliert am Donnerstag (18.10.12) im Deutschen Bundestag in Berlin bei ihrer Regierungserklaerung zum Europaeischen Rat. Merkel hat Griechenland Versaeumnisse bei den versprochenen Reformen vorgeworfen. Die Lage in Griechenland ist alles andere als einfach, sagte sie am Donnerstag in einer Regierungserklaerung im Bundestag. Vieles gehe zu langsam voran, strukturelle Reformen liefen oft nur im Schneckentempo ab. Ausserdem arbeite die Verwaltung an vielen Stellen unzureichend. (zu dapd-Text) Foto: Oliver Lang/dapd***Berlin/ Peer Steinbrueck, frueherer Bundesfinanzminister und designierter SPD-Spitzenkandidat fuer die Bundestagswahl 2013, spricht am Donnerstag (18.10.12) im Bundestag in Berlin. (zu dapd-Text) Foto: Oliver Lang/dapd

ሜርክልና ሽታይንብሩክ

የዩሮ ሸርፍ ተጠቃሚ ሐገራት የገጠማቸዉ ምጣኔ ሐብታዊ ኪሳራ ጀርመን ዉስጥ በመጪዉ ዓመት የሚደረገዉ ምርጫ አብይ የመፎከካሪያ ርዕሥ መሆኑ ከወዲሑ እየታየ ነዉ።ለመራሔ-መንግሥትነቱ የሚወዳደሩት የሁለቱ ትላልቅ የፖለቲካ ማሕበራት እጩዎች ዛሬ በሐገሪቱ ምክር አባላት ፊት ቀርበዉ የምርጫ ዘመቻ ፉክክር የመሠለ የፊት ለፊት ክርክር አድገዋል።በሥልጣን ላይ ያሉት መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል የዩሮን ኪሳራ ለማቃለል ተጣማሪ መንግሥታቸዉ የወሰደዉ እርምጃ ጥሩ ዉጤት አምጥቷል ባይ ናቸዉ። የዋነኛዉ ተቃዋሚ፥ የሶሻል ዲሞክራቶቹ ፓርቲ እጩ መራሔ መንግሥት ፔር ሽታይንማየር የሜርክል አቋምና የመንግሥታቸዉን እርምጃ አጣጥለዉ ነቅፈዉታል። ክርክሩን የታዘቡ እንዳሉት ቀኑ የሽታይንብሩክ ነበር። በሌላ በኩል የአዉሮጳ ኅብረት መሪዎች ብራስልስ ቤልጅግ ላይ ለሁለት ቀናት የሚያካሂዱትን ጉባኤ ርዕሰ ጉዳይ የፈረንሳይና ጀርመን ፍጭት ሊለዉጠዉ እንደሚችል እየተገነገረ ነዉ። የአዉሮጳ ማዕከላዊ ኃይሎች የሚባሉት ሁለቱ ሀገሮች ኅብረቱ የሀገራትን በጀት ይከታተል በሚለዉ የተግባቡ አይመስልም።

የጀርመን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የአዉሮጳ ኅብረት ለሀገራት ከሚተምነዉ ዓመታዊ የበጀት ጉድለት በታች በጀት የሚመድቡ መንግስታትን እንዲቆጣጠርና እንዲቀጣ የሚያስችለዉ ደንብና ስልጣን እንዲኖረዉ ይጠይቃሉ። የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ፍራንሷ ኦሎንድ በበኩላቸዉ በዛሬዉ ጉባኤ በጀትን የሚመለከት አጀንዳ የለም፤ ይልቁንም የአዉሮጳን ባንኮች ህብረት ማጠናከር በሚለዉ ላይ እናተኩር ባይናቸዉ። ሜርክልና ኦሎንድ ልዩነታቸዉን ለማጥበብ ከጉባኤዉ አስቀድሞ የብቻቸዉን ዉይይት እንደሚያደርጉ ተገምቷል። ከጉባኤ አስቀድመዉ ሜርክል በርሊን ላይ ለምክር ቤታቸዉ የዩሮን ቀዉስ አስመልክተዉ ባደረጉት ንግግር የጋራዉ ሸርፍ ለአዉሮፓ አለዉ ያሉትን አንድምታም በዚህ መልኩ ገልፀዋል፤
«ዩሮ ከሌሎች በርካታ መሣሪዎችና ርምጃዎች ጋ ሆኖ ለእኛ ጥንካሬ ነዉ፤ ይህ ዩሮ ከመገበያያ ነትም እጅግ የላቀ ነዉ፤ ይህ ዩሮ በመላ አዉሮጳ ከከፍተኛ ጥቅሙ ጋር በምጣኔ ሃብቱ፤ በማኅበራዊዉ እንዲሁም በፖለቲካዉ ተምሳሌት ሆኖ አዉሮጳን አንድ አድርጎ ይገልፃል።»
ሜርክል ኅብረቱ የገጠመዉን ቀዉስ ለመፍታት ርምጃዎች እንዲፋጠኑም ጠይቀዋል። የዩሮ ቀጣና ቀዉስ ከገጠመዉ ወዲህ የኅብረቱ መሪዎች ዛሬ እና ነገ የሚያካሂዱት ጉባኤ 22ኛቸዉ መሆኑ ነዉ።

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች