የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን የመጀመርያ ግጥምያ | ስፖርት | DW | 12.06.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ስፖርት

የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን የመጀመርያ ግጥምያ

የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ጀርመን ዛሬ ከዩክሬን በምታደርገው ጨዋታ የአውሮጳ ዋንጫ መርሐ ግብሯን አንድ ብላ ትጀምራለች። አንድ አጥቂ እና በርካታ የመሐል ሜዳ ተጨዋቾችን ይዘው ወደ ፈረንሳይ ያቀኑት አሰልጣን ዮአኪም ሎቭ ከቱርክ ጋር በጥንቃቄ ከተጫወቱ አሸናፊ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

አስራ አንድ ጊዜ በአውሮጳ ዋንጫ የተሳተፈችው ጀርመን በምድብ የመክፈቻ ጨዋታ አንድም ጊዜ ተሸንፋ አታውቅም።ውድድሩን በጎሮጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1972, 1980 እና በ1996 አሸናፊ ሆናለች። የጀርመን የመሐል ሜዳ ኃላፊነት የተጣለበት ቶማስ ክሮስ ዩክሬን ቀላል ተጋጣሚ እንዳልሆነ ጠቁሟል።

ቻይናን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት እግር ኳስ አፍቃሪዋ የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል፤ ለሃገሪቱ ብሔራዊ ቡድን መልካም እድልን ተመኝተዋል። የአዉሮጳ የእግር ኳስ ሻንፒዮናና በምታስተናግደዉ በፈረንሳይ በሁለተኛዉ ቀን ጨዋታ በእንጊሊዝና በሩስያ ቡድን ደጋፊዎች መካከል የታየዉን ኃይል የቀላቀለ ከፍተኛ ብጥብጥን ተከትሎ የአዉሮጳ የእግር ኳስ ማኅበር ምርመራ መሠረተ። በዘገባዉ መሠረት የጨዋታ ፊሽካ ከተነፋ በኋላ የሩስያ ደጋፊዎች የእንግሊዝ ደጋፊዎች ወደ ነበሩበት ቦታ በማለፍ ከፍተኛ ጥቃት አድርሰዋል። አንዳንድ የእንግሊዝ ደጋፊዎች እየደረሰባቸዉ የነበረዉን ከፍተኛ ጥቃት ለመከላከል በስታዲዮሙ ዉስጥ በነበረዉ ክፍል በመግባት ለማምለጥ መመኮራቸዉም ተያይዞ ተዘግቦአል። የአዉሮጳ የእግር ኳስ ማኅበር የዲሲፕሊን ኮሚቴ ዉሳኔዉን የፊታችን ማክሰኞ እንደሚያሳዉቅ ገልፆአል። በሁለተኛዉ ቀን በተከሰተዉ በዚህ ግጭት 31 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ አንድ እንግሊዛዊ ደጋፊ በጉዳቱ ለሕይወት አስጊ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ፖሊስ አስታዉቋል።

የአዉሮጳ የእግር ኳስ ማኅበር አሁን ከቅርብ ሰዓታት በፊት ባወጣዉ መግለጫ ደግሞ በእንግሊዝና በሩስያ ደጋፊዎች መካከል ረብሻዉ ከቀጠለ እንጊዝና ሩስያ ከእግር ኳስ ግጥምያዉ ሊታገዱ ይችላሉ ሲል አስጠንቅቋል።

እሸቴ በቀለ

አዜብ ታደሰ