የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ድልና የሽቫይንሽታይገር ስንብት | ስፖርት | DW | 01.09.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ስፖርት

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ድልና የሽቫይንሽታይገር ስንብት

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ለብዙ ዓመታት በአምበልነት የተሰለፈውን እና ከዚሁ ተግባሩ የተሰናበተው ባስትያን ሽቫይንሽታይገርን ትናንት ምሽት ያዘጋጀው የወዳጅነት ግጥሚያ በድል ተጠናቀቀ።


ብሔራዊ ቡድኑ ትናንት ምሽት በጀርመን የመንሽንግላድባህ ከተማ ከፊላንድ ጋር ባደረገዉ የወዳጅነት ግጥምያ 2 ለ 0 በሆነ ዉጤት አሸንፎአል። የስንብት ግጥምያ የተደረገለትና ትናንት በቡድኑ ለመጨረሻ በአንበልነት በመምራት የተጫወተዉ ሽቫይንሽታይገር፤ በብሔራዊ ቡድኑን ወክሎ ሲጫወት የትናንትናዉ 121ኛ ጊዜ መሆኑም ታዉቋል። ባስቲ ሲሉ የሚጠሩትን የተወዳጁን የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አንበል በቡድኑ የመጨረሻ ግጥምያን በሞንሽንግላድባህ በሚገኘዉ ስቲዲዮም ለመከታተል የገባዉ ሰዉ 30 ሺህ እንደሆነም ተመልክቶአል። ሽቫይንሽታይገር በማንችስተር ቡድን ተሰልፎ እንደሚጫወት ይታወቃል።

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic