የጀርመን ቀኝ አክራሪዎች እንቅስቃሴ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 22.11.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመን ቀኝ አክራሪዎች እንቅስቃሴ

መሰረታቸው የውጭ በሆነ ዘጠኝ ሰዎች ና በአንዲት ፖሊስ ላይ እጎአ ከ 2000 እስከ 2007 ዓመተ ምህረት በተለያዩ የጀርመን ከተሞች የደረሱ ግድያዎች በቀኝ አክራሪዎች መፈፀሙ ባላፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከተነገረ ወዲህ የቀኝ አክራሪዎች እንቅስቃሴ እዚህ ጀርመን አብይ የመነገሪያ ርዕስ ሆኗል ።

default

3 ቀኝ አክራሪዎች እነዚህኑ 8 ቱርካውያንና አንድ ግሪካዊን እንዲሁም አንዲት የጀርመን ፖሊስን በዚህ ጊዜ ውስጥ በመግደል ተጠርጥረዋል ። ከመካከላቸው ሁለቱ በቅርቡ የራሳቸውን ህይወት ያጠፉ ሲሆን አንዷ ባልደረባቸው ደግሞ እጇን ለፖሊስ ሰጥታለች ። ሶስቱ ተጠርጣሪዎች ሌሎች ግብረ አበሮች እንደነበሩዋቸውም አንዳንድ መረጃዎች እየወጡ ነው ። ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የጀርመን ባለሥልጣናት ስለ ግድያው ተጨማሪ ምርመራዎች እንደሚካሄዱና የተለያዩ እርምጃዎችንም እንደሚወስዱ ሲያስታውቁ ነው የሰነበቱት ። የጀርመን ዋና ዋና ፓርቲዎችም ቀኝ አክራሪ የሚሉት ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ እንዲታገድ እንቅስቄሴ እንዲጀመር እያሳሰቡ ነው ። ዶክተር መኮንን አሸናፊ የጀርመን መዲና የበርሊን ነዋሪ ናቸው ። ጀርመን ሲኖሩ በርካታ ዓመታት ተቆጥረዋል ። እ.ጎ.አ በ 1990 ዎቹ መጀመሪያ ላይ የቀኝ አክራሪዎች ጥቃት ሲጠናከር የውጭ ዜጎችን በማደራጀት በጀርመን በውጭ ዜጎች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን መቋቋም የሚቻልበትን መንገድ በመንደፍ ባቢሎን የተባለ ድርጅት መስረተው እስካሁን ድረስ በዚሁ ተግባር ላይ የተሰማሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ናቸው ። ባላፉት ዓመታት በውጭ ዜጎች ላይ የደረሱት ግድያዎች በቀኝ አክራሪዎች መፈፀማቸው መታወቁ ምን ጠቀሜታ እንዳለው ጠይቃቸው ነበር ።

ሂሩት መለሰ

አርያመ ተክሌ

Audios and videos on the topic