የጀርመን ሥነሕዝብ ጥናት ድርጅት የወጣቶች ልማት ማዕከል በደብረዘይት | ኤኮኖሚ | DW | 25.11.2004
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

የጀርመን ሥነሕዝብ ጥናት ድርጅት የወጣቶች ልማት ማዕከል በደብረዘይት

ጀርመናውያን ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚያደርጉት የልማት እንቅስቃሴ ተሳትፎ ብዙ ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል። በዚህ ረገድ የግሉም ዘርፍ ተሳትፎ እየተሻሻለ ነው የሄደው። አሁን ደግሞ አንድ በተለይ ለወጣጦች ደህንነት ዓይነተኛ ዓርአያነት ያለው ፕሮዤ ነው የተዘረጋውና ክንውንም ያገኘው።

አሁን በይፋ እንደታወቀው፥ “ዲ-ኤስ-ደብልዩ” የተባለው የጀርመን ዓለምአቀፍ የሥነሕዝብ ጥናት ድርጅት እና ቦኒታ የተሰኘው የጀርመን ጨርቃጨርቅ-እንዱስትሪ-ኩባንያ ተባብረው ኢትዮጵያ ውስጥ መጀመሪያውን የወጣቶች ልማትና ሥልጠና ማዕከል በደብረዘይት አቋቁመዋል። በዛሬው ዝግጅታችን ይህንኑ መሠረት በማድረግ፣ ወኪላችን አሰገደች ይበርታ ቃለምልልስ በማከል ያጠናቀረችውን ዘገባ ነው የምናሰማችሁ። ዘገባውና ቃለምልልሱ እነሆ ቀጥሎ ሊደመጥ ይችላል፥