የጀርመን ምክር ቤት እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅሬታ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 22.10.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመን ምክር ቤት እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅሬታ

በጀርመን ባለፈው መስከረም ወር በተካሄደው ምክር ቤታዊ ምርጫ የብዙኃኑን ድምፅ ያገኙት የክርስትያን ዴሞክራቶች እና የክርስትያን ሶሻል ህብረት፣ ከሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲዎች ጋ በቅርቡ የጥምር መንግሥት ያቋቁማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

እነዚሁ ፓርቲዎች ባንድነት ትልቁን ጥምር መንግሥት ከመሠረቱ ደግሞ መጪው ጊዜ በምክር ቤት ለሚወከሉት ለትንንሾቹ ፓርቲዎች አዳጋች ይሆናል የሚሉ ወገኖች እየተበራከቱ መጥተዋል። ከ631 የምክር ቤት መንበሮች መካከል የተቃዋሚዎቹ የ«አረንጓዴው እና የግራ ፓርቲዎች» ባንድነት 127 መንበሮችን ፣ ቀሪዎቹን 504 ትላልቆቹ ፓርቲዎች የያዙበት ድርጊት በተቃዋሚዎቹ ፓርቲዎች ስራ ላይ እክል ይደቅናል።

ቮልፍጋንግ ዲክ

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic