የጀርመን ምርጫ እጩዎች ክርክር | ዓለም | DW | 14.09.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የጀርመን ምርጫ እጩዎች ክርክር

የጀርመን ምርጫ ሊካሔድ አስራ ሁለት ቀናት ብቻ ቀርተውታል። መስከረም 26 በሚካሔደው ምርጫ ለ16 አመታት ጀርመንን የመሩት መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክልን የሚተካው ፖለቲከኛው ይታወቃል። ከሶሻል ዴሞክራቶቹ ኦላፍ ሾልዝ፣ ከክርስቲያን ዴሞክራቶች ኅብረት አርሚን ላሼት እንዲሁም ከግሪን ፓርቲ አናሌና ቤርቦክ ባለፈው እሁድ ክርክር አድርገዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:45

ጀርመን መስከረም 16 የምክር ቤት ምርጫን ታካሂዳለች

መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልን ለመተካት በምርጫ የሚወዳደሩ ሶስት እጩዎች ባለፈው እሁድ በቀጥታ የቴሌቭዥን ሥርጭት ክርክር ገጥመው ነበር። ከሶሻል ዴሞክራቶቹ ኦላፍ ሾልዝ፣ ከክርስቲያን ዴሞክራቶች ኅብረት አርሚን ላሼት እንዲሁም ከግሪን ፓርቲ ወይም አረንጓዴ ፓርቲ አናሌና ቤርቦክ ሶስቱ እጩዎች ናቸው። 90 ደቂቃ የፈጀው ክርክር ሲጠናቀቅ ኢንፍራቴስት ዲማፕ የተባለው የጥናት ተቋም ካነጋገራቸው 1500 ሰዎች መካከል 41 በመቶው ኦላፍ ሾልዝ የበለጠ አሳማኝ ሆነው እንዳገኟቸው ምላሽ ሰጥተዋል። 27 በመቶው አርሚን ላሼት 25 በመቶው ደግሞ አናሌና ቤርቦክ አሳማኝ ሆነው እንዳገኟቸው መልስ ሰጥተዋል።

የጀርመን ምርጫ ሊካሔድ አስራ ሁለት ቀናት ብቻ ቀርተውታል። መስከረም 26 በሚካሔደው ምርጫ ለአራት የሥልጣን ዘመናት ጀርመንን የመሩት መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክልን የሚተካው ፖለቲከኛው ይታወቃል። ከይልማ ኃይለ ሚካኤል ጋር ለምርጫ ውድድር የቀረቡት ሶስት እጩዎች ባለፈው እሁድ በቴሌቭዥን የቀጥታ ሥርጭት ስላደረጉት ክርክር የተደረገውን ቃለ-መጠይቅ የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያዳምጡ

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ

Audios and videos on the topic