የጀርመን ምርጫ፦ በፍራንክፈርት የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 26.09.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመን ምርጫ፦ በፍራንክፈርት የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች

ጀርመናዊቷ ኮርልሊን ሲመርማን "አንገብጋቢው እና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አያሌ ሰዎች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ስለሚገኙ የእነሱ ሕይወት የሚሻሻልበትን መንገድ መሻት ነው። የሰዎች ሰብዓዊ መብት መከበር ጉዳይም በአውሮፓ ኅብረት ጭምር እንዲረጋገጥ እና የውጭ ግንኙነት ፖለቲካውም እንዲጠናከር ለውጥ የሚያመጣ ፓርቲ መምረጥ ያስፈልጋል" ሲሉ ተናግረዋል

ጀርመናውያን ዛሬ በተከናወነው ብሔራዊ ምርጫ ድምጻቸውን ሲሰጡ ውለዋል

በምርጫው የአንጌላ ሜርኪል መሀል ግራው የክርስትያን ዲሞክራት ህብረት ፓርቲ ተጣማሪ መንግስት ለመመስረት ከመሐል ቀኙ ሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ ብርቱ ፉኩክር እንደሚጠብቀው ተገልጿል። የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች በተከታታይ ካደረጓቸው የቀጥታ የቴሌቪዥን ክርክር በኋላ በተደረገ የቅድመ ምርጫ የመራጮች አስተያየት ተሰባስቧል።

ጀርመናዊቷ ኮርልሊን ሲመርማን "በእኔ በኩል አንገብጋቢው እና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አያሌ ሰዎች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ስለሚገኙ የእነሱ ሕይወት የሚሻሻልበትን መንገድ መሻት ነው። የሰዎች ሰብዓዊ መብት መከበር ጉዳይም በአውሮፓ ኅብረት ጭምር እንዲረጋገጥ እና የውጭ ግንኙነት ፖለቲካውም እንዲጠናከር ለውጥ የሚያመጣ ፓርቲ መምረጥ ያስፈልጋል" ሲሉ ለዶይቼ ቬለው እንዳልካቸው ፈቃደ ተናግረዋል።

ከፍራንክፈርት አጠገብ በምትገኘው አልተንሽታት የተባለች አነስተኛ ከተማ የሚኖሩት እና አቶ አንቀሳዊ ምስጋኑ "ለእኔ እንደ ምርጫ ልወስደው የምችለው የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ የተሻለ የፖለቲካ አካሔድ አለው የሚል ዕምነት አለኝ" ሲሉ ብለዋል።

በጀርመን ፌድራል ስታስቲክስ ቢሮ መረጃ መሠረት ከአገሪቱ 83 ሚሊዮን ዜጎች መካከል 60.4 ሚሊዮን መምረጥ ይችላሉ። ከዚህ ውስጥ 31.2 በመቶው ሴቶች ሲሆኑ 29.2 በመቶ ወንዶች ናቸው። በጎርጎሮሳዊው 2017 ዓ.ም. በተካሔደው የምክር ቤት ምርጫ 61.7 ሚሊዮን ዜጎች የመምረጥ መብት ነበራቸው።

ባለፉት አራት አመታት ወደ 2.8 ሚሊዮን ገደማ ጀርመናውያን 18 አመት ሞልቷቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በመካሔድ ላይ በሚገኘው ምክር ቤታዊ ምርጫ ድምጽ የመስጠት ሕጋዊ መብት ባለቤት ሆነዋል። ይኸ ከአጠቃላይ የመራጮች ቁጥር ወደ 4.6 በመቶ መሆኑ ነው። በንጽጽር 21.3 በመቶ መራጮች ዕድሜያቸው 70 እና ከዚያ በላይ ነው።

እንዳልካቸው ፈቃደ

እሸቴ በቀለ

ሒሩት መለሰ

ታምራት ዲንሳ