የጀርመን ምርጫ-ልዩነቱ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 10.09.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመን ምርጫ-ልዩነቱ

ፒር ሽታይንቡርክ ያንን መርሕ ያኔ ካስረቀቁት ባለሥልጣናት አንዱ ነበሩ።እሳቸዉና ብጤዎቻቸዉ መርሑን ሲርቁን አንጌላ ሜርክል እያተረፉበት ነዉ።ሽታይንብሩክና ፓርቲያቸዉ ባሁኑ ምርጫ ከሜርክልና ከፓርቲያቸዉ የሚለይቡት የጎላ መርሕ ወይም እቅድ በጣም ትንሽ ነዉ።የሠራተኞች የሰዓት ክፍያ ነዉ።

BERLIN, GERMANY - SEPTEMBER 01: In this screenshot taken from German television German Chancellor and Christian Democrat (CDU) Angela Merkel and Social Democrats (SPD) chancellor candidate Peer Steinbrueck debate live at the Adlershof studios on September 1, 2013 in Berlin, Germany. Today's live debate is the only one between the two candidates ahead of German elections scheduled for September 22. (Photo by Sean Gallup/Getty Images)

ተፎካካሪዎቹ

23 08 13

በንድፈ-ሐሳብ ደረጃ መሥከረም አሥራ-ሁለት ጀርመን ዉስጥ የሚደረገዉ ምርጫ ዉጤት የዚያኑ ዕለት ማታ እስኪታወጅ ድረስ የሚሆነዉ አይታወቅም።በተጨባጭ ግን መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ለተጨማሪ ዘመነ-ሥልጣን ለመመረጥ ከፍተኛ ድጋፍ እንዳላቸዉ ከወዲሁ በግልፅ ይታወቃል። የዋነኛዉ ተቃዋሚ የሶሻል ዲሞክራቶቹ ፓርቲ (SPD) ዕጩ ፒር ሽታይንብሩክ የወይዘሮ አንጌላ ሜርክልን መንበር ለመረከብ በሁሉም ግንባር የከፈቱትን ዘመቻ አጧጡፈዉታል።ፎልከር ቫግነር እንደታዘበዉ ወቅቱ ለሚጠይቀዉ ጉዳይ ሽታይንብሩክ ተገቢዉ ሰዉ ናቸዉ።ከሚፈልጉት መድረሳቸዉ ግን ሲበዛ አጠራጣሪ ነዉ።የቫግነርን ዘገባ ነጋሽ መሐመድ አጠናቅሮታል።


የገንዘብ ጉዳይ አዋቂ ናቸዉ።የፌደራላዊዉን መንግሥት የበጀት ጉድለትን ከነምክንያቱ ጠንቅቀዉ ያዉቃሉ።የክርስቲያን ዴሞክራቶች/ የክርስቲያን ሾሻሎቹ ሕብረት (CDU/CSU) ከሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲ SPD ጋር መሥረተዉት የነበረዉ ታላቅ ተጣማሪ መንግሥት የገንዘብ ሚንስትር ነበሩ።በዚያ የዓለም ምጣኔ ሐብት በተሽመደመደበት ወቅት ጀርመንን ከከፋ ኪሳራ አድነዉ ዛሬ-ላለችበት ጥንካሬ መሠረት ጥለዋል።መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክልንም በታማኝነት አገልግለዋል።ፒር ሽታይንብሩክ።አሁን ግን የአለቃቸዉን መንበር በምርጫ ወርሰዉ ራሳቸዉ አለቃ መሆን ነዉ-ፍላጎት፥ አላማ ትግላቸዉ።

«የጀርመን ፌደራላዊ ሪፐብሊክ መራሔ-መንግሥት መሆን እፈልጋለሁ።»

ይሁንና በሥልጣን ላይ ካሉት መራሒተ መንግሥት ጋር የሚያደርጉት ፉክክር «የኩያ» የሚባል አይነት አይደለም።የሕዝብ አስተያየት ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ሽታይንብሩክ ከሜርክል ጋር ሲነፃፃር ያላቸዉ ድጋፍ በጣም ትንሽ ነዉ።ለዚሕ ብዙ ምክንያቶች አሉ።ጥቆቶቹ፥ ዉድድሩ የሚደረገዉ ሜርክል ከሥልጣናቸዉ የመጨረሻ ጫፍ ላይ በደረሱበት ወቅት መሆኑ ነዉ።ፓርቲያቸዉን ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠራሉ።

በዩሮ-ኪሳራና ዕዳን በመቆጣጠር አሠራራቸዉ በብራስልስ መርሕ ላይ ከፍተኛ ተፅኖ ያሳርፋሉ።በዚሕ ምክንያት ከአብዛኞቹ ጀርመኖች አክብሮትና አድናቆት አትርፈዋል።ሽታይንብሩክና ፓርቲያቸዉ ((SPD) ጠንካራ አጥቂዎቻቸዉን መልሰዉ ማጥቃት ቀርቶ፥ የመገናኛ ጉዳይ ባለሙያዉ ክርስቶፍ ሞስ እንደሚሉት በቅጡ መከላከል እንኳ የሚያስችል ሥልት ያላቸዉ አይመስልም።
ድምፅ
«SPD፣ (የመንግሥት ምግባር) ሁሉም መጥፎ ነዉ ይላል።ጀርመኖች ግን (በመንግሥት) በጣም ደስተኞች ናቸዉ።»

ሞስ እንደሚሉት መራጮች ሽታይንብሩክና ፓርቲያቸዉ በምርጫዉ ቢያሸንፉ የሚያደርጉትን በግልፅ ማወቅ ይፈልጋሉ።ሶሻል ዲሞክራቶቹ እስካሁን ያቀረቡና የሚያቀርቡት አማራጭ ግን ባብዛኛዉ መረጭ በተለይም በደጋፊዎቻቸዉ ዘንድ ብዙም ተወዳጅነት የለዉም።

እርግጥ ነዉ ከሜርክል በፊት መራሔ መንግሥት የነበሩት የSPDዉ ፖለቲከኛ ጌርሐርድ ሽሮደር የነደፉት «አጀንዳ 2010 » የተሰኘዉ የምጣኔ ሐብት መርሐቸዉ ዓለምን ያፍረከረከዉ የምጣኔ ሐብት ድቀት ጀርመንን ብዙ ሳይነካት እንዲያልፋት ረድቷል።ይሁንና መርሑ የማሕበራዊ ዋስትናን፥ የአነስተኛ ገቢ ድጎማን፥ የጡረታ አበልን እና የመሳሰሉትን ጥቅማጥቅሞች በመቀነሱ ለወትሮዉ ለሠራተኛዉ ወይም ለአነስተኛዉ መደብ የሚወግነዉን SPDን ከደጋፊዎቹ አርቆበታል።

ግራዉን የፖለቲካዊ አስተሳሰብ ጠንከር አድርገዉ የሚከተሉት አንዳድ የፓርቲዉ መሪዎችና አባላት ሽሮደርና ተባባሪዎቻቸዉ የሚመሩትን ፓርቲያቸዉን ጥለዉ ሌላ ፓርቲ የመሠረቱትም ለዚሕ ነዉ።የመሐል-ቀኝ ዘመሙ የአንጌላ ሜርክል ፓርቲና መንግሥት የሽሮደሩን SPD የኢኮኖሚ መርሕን በሚሹት መንገድ አርቀዉ ገቢር አድርገዉ ደጋፊ ሲያፈሩበት የዘመኑ የSPD መሪዎች ግን በደጋፊዎቻችን እንጠላለን በሚል ሥጋት የሾሮደር መንግሥት ከቀየሰዉ መርሕ እራሳቸዉን እያገለሉ ነዉ።

KOMBO - SPD-Kanzlerkandidat Peer Steinbrück und Bundeskanzlerin Angela Merkel reden am 03.09.2013 während der Sitzung des Bundestags in Berlin. Weniger als drei Wochen vor der Wahl ist der Bundestag zu seiner voraussichtlich letzten Sitzung zusammengekommen. Foto: Hannibal/dpa

ሽታይንብሩክና ሜርክል

የሐይድልበርጉ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ፕሮፌሰር ኤድጋር ቮልፍሩም እንደሚሉት እንዲሕ አይነቱ አቋም የፓርቲዉን መርሕ እዉቅና ከመንፈግ ይቆጠራል።

«ችግሩ፥ SPD እራሱን ከቀድሞዉ መንግሥት እርምጃና መርሕ ማራቁ ነዉ።በመሠረቱ እንዲሕ አይነቱ አቋም ከ1998 እስከ 2005 (ሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅት) የተከተለዉን መርሕ ሕጋዊነት ማፍረስ ነዉ።»

ፒር ሽታይንቡርክ ያንን መርሕ ያኔ ካስረቀቁት ባለሥልጣናት አንዱ ነበሩ።እሳቸዉና ብጤዎቻቸዉ መርሑን ሲርቁን አንጌላ ሜርክል እያተረፉበት ነዉ።ሽታይንብሩክና ፓርቲያቸዉ ባሁኑ ምርጫ ከሜርክልና ከፓርቲያቸዉ የሚለይቡት የጎላ መርሕ ወይም እቅድ በጣም ትንሽ ነዉ።የሠራተኞች የሰዓት ክፍያ ነዉ።SPD ከመተመረጠ ዝቅተኛዉ የሠራተኛ ደሞዝ በሰዓት 8. ዩሮ ከ50 እንዲሆን እወስናለሁ ባይ ነዉ።CDU ክፍያ መወሰን ያለበት በአሠሪና ሠራተኞች ሥምምነት ነዉ።SPDየማሕረዊ ድጎማ ሊያጠናክር አቅዷል።CDU ይሕን አይቀበለዉም።በሁለቱ ትላልቅ ፓርቲዎች መርሕ መካካል ያለዉ ልዩነት መጥበብ ሜርክል ያላቸዉን ድጋፍ ይበልጥ

አጠናክሮላቸዋል።

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic