የጀርመን መራሂተ መንግስት የዩኤስ አሜሪካ ይፋ ጉብኝት | ዓለም | DW | 07.06.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የጀርመን መራሂተ መንግስት የዩኤስ አሜሪካ ይፋ ጉብኝት

የጀርመን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በዩኤስ አሜሪካ ልዩ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

default

አምስት ሚንስትሮች ይዘው ትናንት ወደ ዩኤስ አሜሪካ የተጓዙት ሜርክልከፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ጋ በአፍጋኒስታን እና በሊቢያ እንዲሁም በበርካታ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ። ዛሬ ማታ በዋይት ሀውስ ቤተመንግስት ለመራሂተ መንግስት ሜርክል ክብር በሚደረገው ይፋ የራት ግብዣ ላይ ፕሬዚደንት ኦባማ ለጀርመናዊትዋ መራሂተ መንግስት በዩኤስ አሜሪካ ለአንድ ሲቭል የሚሰጠውን ከፍተኛ የነጻነት ሜዳልያ ይሸልማሉ።

አበበ ፈለቀ

አርያም ተክሌ