የጀርመን ሕገ-መንግሥት 65ኛ ዓመት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 23.05.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመን ሕገ-መንግሥት 65ኛ ዓመት

ሕገ-መንግሥቱ ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ የተቆጠሩት 65 ዓመታት በጀርመን ታሪክ አቻ የማይገኝላቸዉ ድሎች የተመዘገበበት ጊዜ ነዉ

የጀርመን ሕገ-መንግሥት የፀደቀበት ሥልሳ-አምስተኛ ዓመት ዛሬ ጀርመን ዉስጥ ታስቦ ዉሏል።ሕገ-መንግሥቱ ከናትሲ አምገነናዊ ሥርዓት የተላቀቀችዉ ጀርመን የዜጎች መብት የተከበረባት፤ ፍትሕና ዴሞካራሲያዊ ሥርዓት የፀናባት ሐገር እንድትሆን ጠንካራ መሠረት የጣለ መሆኑ በሰፊዉ እየተነገረ ነዉ።የጀርመን የሕግ-መምሪያ እና የሕግ-መወሰኛ ምክር ቤት አባላት ዕለቱን በጋራ አክብረዉታል።የሕግ-መወሰኛዉ ምክር ቤት ( Bundeserat) ፕሬዚዳንት፤ የኒደርዛክሰን ሚንስትር ፕሬዝዳንት ሽቴፋን ቫይል እንዳሉት ሕገ-መንግሥቱ ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ የተቆጠሩት 65 ዓመታት በጀርመን ታሪክ አቻ የማይገኝላቸዉ ድሎች የተመዘገበበት ጊዜ ነዉ።የሕግ-መምሪያዉ ምክር ቤት (Bundesetage) ፕሬዚዳንት ኖርበርት ላሜርት በበኩላቸዉ እንዳሉት ሕገ-መንግሥቱ ከጀርመን አልፎ ለሌሎች ዴሞክራሲያዊ ሥራዓትን ለሚገነቡ ሐገራትም አብነት ነዉ።

« ከዓለም ትላልቅ ሕገ-መንግሥታት አንዱ ከሆነ ቆየ።ለታዳጊ ዴሞክራሲዎች አቅጣጫን የሚያመላክት፤ በሐገር ደረጃም ለሌች ሕገ-መንግሥቶች እንደ ማጣቃሻ ምሳሌ የሚያገለግል ነዉ።»

የፌደራል ጀርመን ሪፐብሊክ እስካሁን የሚሠራበት ሕገ-መንግሥትን በይፋ ያፀደቀችዉ ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት አሸናፊዎች ቀጥታ ቁጥጥር በተላቀቀች ማግሥት እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር በ1949 ነበር።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ