የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት የኢትዮጵያ ጉብኝት | ኢትዮጵያ | DW | 11.10.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

 የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት የኢትዮጵያ ጉብኝት

የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ከትናንት ማታ ጀምሮ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀቁ።  ሜርክል ዛሬ ከቀትር በፊት ከኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር  ከተነጋገሩ በኋላ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:59
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
02:59 ደቂቃ

የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ


ሜርክል በሃገሪቱ የተቃዉሞ ሰልፍ ሊፈቀድ ይገባል ፤ ፖሊስ የሚወስደዉ እርምጃም ተመጣጣኝ ሊሆን ይገባል ብለዋል። የመንግሥት ተቃዋሚዎች በሃገሪቱ ፖለቲካ ሊሳተፉ እንደሚገባም ተናግረዋል።  መራሂተ መንግሥቷ ከቀትር በኋላ የአፍሪቃን ኅብረት በመጎብኘት በጀርመን መንግሥት ድጋፍ የተገነባውን የአፍሪቃ ኅብረት የሠላም እና የፀጥታ ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ሕንጻን መርቀዋል።

የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በመጪው የጎርጎሮሳዊው ዓመት በቡድን 20 ፕሬዝዳንትነታቸው ለአፍሪቃ ጉዳይ ቅድሚያ እንደሚሰጡ አስታወቁ ። ሜርክል ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘው የአፍሪቃ ህብረት ፅህፈት ቤት ተገኝተው

ባሰሙት ንግግር በበጎርጎሮሳዊው 2017 አጋማሽ ላይ የኢንዱስትሪዎች ተወካዮች እና ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች የሚካፈሉበት አፍሪቃ ላይ ያተኮረ ጉባኤ በርሊን ውስጥ እንደሚካሄድም ተናግረዋል።  ለአፍሪቃ ዘላቂ እድገት እና የሥራ እድል ፈጠራ በአፍሪቃ የግል ውረታ እንዲጠናከር የሀገራቸው ፍላጎት መሆኑንም ሜርክል ገልፀዋል ። በክፍለ ዓለሙ መሠረተ ልማቶችን ማስፋፋት እና ሙያዊ ሥልጠናዎችንም ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል ።ሜርክል በንግግራቸው የአፍሪቃ ሀገራት ጽንፈኛ ሙስሊም ተዋጊዎችን እና ህገ ወጥ ስደትን ከአሁኑ በበለጠ እንዲዋጉም ጠይቀዋል ። የአሸባሪዎችን እንቅስቃሴ ለመግታትም ዴሞክራሲያዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ተሃድሶዎችን ተግባራዊ እንዲያደርጉም አሳስበዋል ።ህብረቱ የሊቢያውን ግጭት ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥም እንዲሳተፍ ጠይቀዋል ። ሜርክል በዛሬው የአፍሪቃ ህብረት ጉብኝታቸው በጀርመን መንግሥት ድጋፍ የተገነባውን የአፍሪቃ ህብረት የሰላም እና የፀጥታ ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ህንጻን መርቀዋል ። 

 

ዮኃንስ ገ/እግዚአብሔር

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ   

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች