የ«ጀርመንዊንግስ» አይሮፕላን አደጋ መንሥዔን የማጣራቱ ሥራ | ዓለም | DW | 25.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የ«ጀርመንዊንግስ» አይሮፕላን አደጋ መንሥዔን የማጣራቱ ሥራ

የጀርመናውያኑ አየር መስመር «ጀርመንዊንግስ፣ ኤ 320 ኤርባስ » አይሮፕላን፣ ትናንት በደቡብ ፈረንሳይ በአልፕስ ተራራ በምትገኘው የባርሰሎኔት አካባቢ በተከሰከሰበት አሳዛኝ አደጋ 150 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በአደጋው ከሞቱት 72 ጀርመናውያን እና 51 ስጳኛውያን ሌላ፣ የብሪታንያ፣ ዴንማርክ፣

ቤልጅየም፣ ኢራን፣ አውስትሬሊያ፣ እስራኤል፣ ሜክሲኮ፣ ቬኔዝዌላ፣ ኮሎምቢያ፣ አርጀንቲንያ፣ ጃፓን እና የዩኤስ አሜሪካ ዜጎችም ይገኙበታል። የጀርመን ካቢኔ ሟቾቹን ዛሬ በአንድ ደቂቃ የኅሊና ፀሎት ከማሰቡ ጎን፣ በሀገሪቱ ሰንደቃላማዎች በግማሽ እየተውለበለቡ ነው። ስጳኝም የሶስት ቀናት ሀዘን አውጃለች።

አይሮፕላኑ በምን ምክንያት እንደወደቀ መረጃ ሊሰጥ የሚችለው ንዑስ ጥቁር ሣጥን ብልሽት ቢያጋጥመውም መጠቆሙ አይቀርም ይሆናል ሲሉ የፈረንሳይ የሀገር አስተዳደር ሚንስቴር ፣ ሚንስትር ደኤታ አላቪዳሊስ ገልጸዋል።

Frankreich Absturz Germanwings A320 Trauer (Pressekonferenz in in Seyne-les-Alpes)

የአደጋውን ቦታ አካባቢ የጎበኙት ጀርመን፣ የስጳኝ እና የፈረንሳይ መሪዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ

ወድቆ በተከሰከሰው ጀርማን ዊንግስ ተሳፍረው የነበሩት አብዛኞቹ ፤ በጀርመን ፣ የኖርድራይን ቬስትፋለን ፌደራል ክፍለ ክፍለ ሀገር ተወላጆች ሲሆኑ ፤ 16 ቱ ለትምህርት ልውውጥ ሃልተርን ከተባለች ንዑስ ከተማ ባርሴሎና ደርሰው በመመለስ ላይ የነበሩ ለጋ ወጣቶች ነበሩ። የሐልተርን ከተማ ከንቲባ ቦዶ ክሊምፐል ፣

«ከተማይቱ በሐዘን መዋጧን መናገር እፈልጋለሁ። በየሥፍራው ብርቱ ድንጋጤና ሐዘን ነው ከሰው ፊት የሚነበበው።ያጋጠመው ሁኔታ እጅግ አስከፊ መሆኑን ማንም መገመት ይችላል።»

በፈረንሳይ የተከሰተውን የአይሮፕላን አደጋ ለማጣራት እየተደረገ ስላለው ርምጃ የፓሪሷን ወኪላችን ሀይማኖት ጥሩነህን ስቱድዮ ከመግባታችን በፊት በስልክ አነጋግሪያት ነበር።

ሀይማኖት ጥሩነህ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic