የጀርመንና የዩናይትድ ስቴትስ ግንኙነት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 14.07.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመንና የዩናይትድ ስቴትስ ግንኙነት

ጀርመን በመከላከያና በስለላ ተቋሞቿ የሚሠሩ ሁለት ዜጎቿ ለዩናይትድ ስቴትስ መረጃ እንደሚያቀብሉ ከደረሰችበት ወዲህ ከአሜሪካ ጋ የነበራት ጠንካራ ግንኙነት ጥያቄ ላይ የወደቀ እንደመሰለ ነዉ።

በስለላ ከሚገኙ መረጃዎች የመጠቃቀሙ የተጓዳኝነት ምስጢር ልዉዉጥ እንዳለ ሆኖ አንዱ መንግስት ሌላዉን በማይገምተዉ መንገድ መሰለሉ የጀርመንን ፖለቲከኞች ማነጋገሩን ቀጥሏል። ለረዥም ዓመታት ዩናይትድ ስቴትስና ጀርመን እጅግ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸዉ ተጓዳኞች በመሆናቸዉም ዘመን በተሻገረዉ ጉድኝታቸዉ ላይ ተፅዕኖ ሊኖረዉ ይችል አይችል እንደሁ ግን ዝምታን በመረጠችዉ ዋሽንግተንና ምላሽ እንዲሰጣት በምትወተዉተዉ በርሊን መካከል ለጊዜዉም ቢሆን መጠራጠርን ያስከተለ መስሏል። የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለስልጣን ግን ትናንት ምንም ቢፈጠር ትስስሩ እንደማይበጠስ ነዉ ያመለከቱት። ሸዋዬ ለገሠ ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘዉ ወኪላችን አበበ ፈለቀን በጉዳዩ ላይ በስልክ አነጋግራዋለች።

አበበ ፈለቀ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic