የጀርመንና የብራዚል የግማሽ ፍፃሜ ግጥምያ | ስፖርት | DW | 08.07.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ስፖርት

የጀርመንና የብራዚል የግማሽ ፍፃሜ ግጥምያ

በአጓጊነቱ የቀጠለዉ ብራዚል ላይ እየተካሄደ ያለዉ የዓለም የእግር ኳስ ግጥምያ ዛሬ በአስተናጋጅ ሀገር ብራዚል እና በጀርመን መካከል ጀምሮአል። ግጥምያዉ በጀርመን በጉጉት እየተጠበቀ ነዉ

በግማሽ ፍፃሜው ላቲን አሜሪካዉያኑ ሁለት ሀገራትና ከመሃል አዉሮጳ ሁለት ሀገር ለግጥምያ በመቅረባቸዉ ዉድድሩን ለየት አድርጎታል።
ባለፈዉ ሳምንት መጠናቀቅያ ላይ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለመግባት የተጋጠሙት አርጀንቲና እና ቤልጂየም አንድ- ለባዶ መለያየታቸዉ ይታወሳል ። የአርጀንቲናዉ ጎንዛሎ ሂጎይን ስምተኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ግብ ቡድኑን ወደ ግማሽ ፍፃሜ አድርሶታል። አምስት ሰዓት ላይ የተጋጠሙት ሆላንድና ኮስታሪካ ለግማሽ ፍጻሜዉ መለያ መደበኛ የግጥምያ ሰዓታቸዉን አጠናቀዉ በፍፁም ቅጣት ሆላንድ 4 ለ 3 በማሸነፍ ለቀጣይ ዉድድር ቡድኑን የተቀላቀለዉ። በዚህም በግማሽ ፍፃሜው ላቲን አሜሪካዉያኑ ከአዉሮጳዉያኑ ሀገራት ጋር ይጋጠማሉ። ዛሪ ማክሰኞ ጀርመን ከዓለም ዋንጫ ዉድድር አዘጋጅዋ ከብራዚል፤ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 5 ሰዓት ፤ ነገ ረቡዕ ደግሞ ሆላንድ ከአርጃንቲና ለፍፃሜዉ ለማለፍ ይተናነቃሉ።የብራዚልና የጀርመን ብሄራዊ የእግርኳስ ቡድን እንዴት ይገመገማል በቼክ ሪፐብሊክ የአንድ ከተማ የእግር ኳስ አስልጣኝ የሆኑት ዶክተር ተስፋዬ ጥላሁንን ስቱድዮ ከመግባታችን በፊት አነጋግረናቸዉ ነበር።


አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic