የጀርመናዊው ባለሃብት ዕቅድ በኢትዮጵያ | ኤኮኖሚ | DW | 29.07.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኤኮኖሚ

የጀርመናዊው ባለሃብት ዕቅድ በኢትዮጵያ

​​​​​​​የቀድሞ የፍራንክፈርት ከተማ የፓርላማ አባል እና የዓለማቀፍ የጀርመን የኢንቨስትመንት የኢኮኖሚ ልማትና የሙያ አማካሪ ተቋም ባለቤት ጀርመናዊው ዶክተር ዌልከር ማንፍሬድ ፍሎሪያን በኢትዮጵያ ከ10 -300 ሚልዮን ዩሮ በሚገመት ወጪ ዘመናዊ ማሰልጠኛ ተቋም እንዲሁም ልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት ስራዎችን ለማከናወን ማቀዳቸውን ገለፁ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 09:22

የጀርመናዊው ባለሃብት ዕቅድ በኢትዮጵያ

የቀድሞ የፍራንክፈርት ከተማ የፓርላማ አባል እና የዓለማቀፍ የጀርመን የኢንቨስትመንት የኢኮኖሚ ልማትና የሙያ አማካሪ ተቋም ባለቤት ጀርመናዊው ዶክተር ዌልከር ማንፍሬድ ፍሎሪያን በኢትዮጵያ ከ 10 -300 ሚልዮን ዩሮ በሚገመት ወጪ ዘመናዊ የትምህርት ማሰልጠኛ ተቋም እንዲሁም ልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት ስራዎችን ለማከናወን ማቀዳቸውን ገለፁ። 
ባለሃብቱ በተለይ ለዶይቼ ቨል "DW" እንዳብራሩት ፤ ታሪካዊት ሀገር ባሏት ኢትዮጵያ የሁለቱን ሀገራት ቀደምት ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋጋር በሚገነባው ግዙፍ የትምህርት ተቋም የጀርመን ቋንቋ፣ የቴክኒክ፣ የህክምና ፣የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ዘመናዊ የሴኪውሪት አገልግሎትን ጨምሮ የልዩ ልዩ ሙያዎች ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ለሚያስመዘግቡ ተማሪዎችም በጀርመን ዩኒቨርሲቲዎች ፣ ታዋቂ ድርጅቶችና ተቋማት ውስጥ ተጨማሪ ስልጠና እና ትምህርት የሚያገኙበት መንገድ ይመቻቻል ብለዋል።
ዶክተር ዌልከር ላለፉት 30 ዓመታ በዓለም ዙሪያ ከ 63 በሚልቁ ሀገራት በላይ ተዘዋውረው ከአበዳሪ ባንኮች እና ከየሀገራቱ መንግስታት ጋር በተደረሰ ስምምነት ከ 50 ሚልዮን እስከ 1 ቢልዮን ዩሮ ወጪ የተደረገባቸውን ልዩ ልዩ የማሰልጠኛ ተቋማት፣ የኢንዱስትሪዎች ግንባታ እና የኢንቨስትመንት ማስፋፋት ስራዎችን አከናውነዋል።

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ 

እንዳልካቸው ፈቃደ

እሸቴ በቀለ

Audios and videos on the topic