የጀርመናዉያን፣ በስራ ታታሪነትና የቀጠሮ አክባሪነት ባህል | ባህል | DW | 17.11.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የጀርመናዉያን፣ በስራ ታታሪነትና የቀጠሮ አክባሪነት ባህል

አንድ አባት ልጃቸዉን ለመጠየቅ ወደ እዚህ፣ ወደ ጀርመን አገር ብቅ ብለዉ ኖሮ ወደ አገር ቤት ተመልሰዉ ስለ ጀርመርመናዉያኑ ሲገልጹ አሉ፣ ጀርመን በተለይ በተለይ ያ ጠንካራ መርሰዲሳቸዉ የሚያመርቱት ከኒናቸዉ መቼም ልዩ ነዉ! ህዝቡ ታድያ በጣም ቢራ ይወዳል!

default


እንደ ዉሃ ነዉ፣ የሚጠታዉ! ነገሩ በመኺናዉ እና በከኒኑ ይብለጡ እንጂ በቢራዉስ፣ የኛን ጠላ ጠጅ የሚደርስበት የለም። ምግቡም ቢሆን አንቱ የሚባል አይደም አሉ። አሉ! ጀርመናዉያን በሚያመርቱት መኪና፣ የአዉሮፕላን ሞተር፣ በመድሃኒታቸዉ እና በሌሎች ምርታቸዉ ታዋቂ ቢሆኑም፣ ጠንካራ ሰራተኛ ቀጠሮ አክባሪ፣ መሆናቸዉ ይነገርላቸዋል፣ ህዝቡም ጠንክሮ መስራትን እና ጥንቁቅነትን ባህሉ እንዳደረገ ይናገራል። የዛሪዉ የባህል መድረካችን ስለጀርመናዉያኑ የቀጠሮ ማክበር፣ የታታሪ ሰራተኝነት፣ ባህል በጥቂቱ ሊያስቃኘን ተዘጋጅቶአል መልካም ቆይታ