የጀርመኑ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝታቸዉን ጀመሩ | ኢትዮጵያ | DW | 28.01.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጀርመኑ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝታቸዉን ጀመሩ

ትናንት ምሽት ኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ የገቡት የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት ጀምረዋል። ፕሬዚደንት ሳህለ ውርቅ ዘውዴ ከጀርመኑ ፕሬዚዳንት ቫልተር ሽታይንማየር ጋር ተወያዩ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫም ሰጥተዋል።

ትናንት ምሽት ኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ የገቡት የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት ጀምረዋል። ፕሬዚደንት ሳህለ ውርቅ ዘውዴ ከጀርመኑ ፕሬዚዳንት ቫልተር ሽታይንማየር ጋር ተወያዩ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫም ሰጥተዋል።  የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የጀርመኑን ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር በብሔራዊ ቤተ -መንግስት  ዉስጥ ባደረጉት ዉይይት ሃገራቱ በሁለትዮሽ እና ተያየዥ ጉዳዮች ዙሪያ መነጋገራቸዉ ነዉ የተገለፀዉ።

 ኢትዮጵያ ከጀርመን ጋር በንግድና ኢንቨስትመንት ዙሪያ  በጋራ ጥቅም በትብብር ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት ፍላጎት መኖሩም ተመልክቶአል። የጀርመኑ ፕሬዚዳንት  ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ሃገራቸዉ በንግድ፣በኢንቨስትመንት፣በስልጠናና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብርና በቅርበት የምትሰራ መሆኑን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል። የጀርመኑ

ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝታቸዉን መጀመራቸዉ በፊት ጀርመን ላይ በሰጡት ቃለ ምልልስ «ይሕችን ጥልቅ ትርጉም ያላትን ታላቅ አፍሪቃዊት ሐገር በከፍተኛ ፍላጎት እና በታላቅ አክብሮት የምናያት መሆኑን መናገር እንችላለን።አሁን የሚታየዉ (ለዉጥ) በተለይም የለዉጡ አወንታዊ ዉጤቶች፣ ወደ ዴሞክራሲና ምጣኔ ሐብታዊ መረጋጋት የሚደረግ በአካባቢዉም የሚንፀባረቅ ፣ለመላዉ አፍሪቃም በጎ አስተምሕሮ ነዉ።» ብለዉ ነበር።

 


አዜብ ታደሰ