የጀርመኑ ፕሪዝደንት የአፍጋኒስታን ጉብኝት | ዓለም | DW | 16.10.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የጀርመኑ ፕሪዝደንት የአፍጋኒስታን ጉብኝት

የጀርመኑ ፕሪዝደንት ክርስትያን ዎልፍ በአፍጋኒስታን ያልተጠበቀ ይፋ ጉብኝት አደረጉ። ፕሪዝደንት ዎልፍ በአፍጋኒስታን ከፕሪዝደንት ሃሚድ ካርዛይ እና ከሲቢል ተቋማት ተጠሪዎች ጋር እንደሚወያዪ ተነግሮአል።

default

ፕሪዝደንቱ ዋና መዲናዋ ካቡል እንደደረሱ በወታደራዊ ክብር አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በ 44 አመት ግዜ ዉስጥ አንድ የጀርመን ፕሪዝደንት አፍጋኒስታንን ሲጎበኝ የዛሪዉ የፕሪዝደንት ክርስትያን ዎልፍ ጉብኝት የመጀመርያዉ እንደሆነም ተመልክቶአል። የጀርመኑ ፕሪዝደንት ካቡል አቀባበል ከተደረገላቸዉ በኋላ ባሰሙት ንግግር አገራቸዉ እ.ጎ.አ 2014 አ.ም የአፍጋኒስታንን የጸጥታ ጥበቃ ስራ ለአገሪቷ ሙሉ በሙሉ ካስረከበች በኋላም ታማኝና ዘላቂ የሆነ የወዳጅነት ግንኙነት እንደሚኖራት ገልጸዋል። ፕሪዝደንቱ በዚህ ጉብኝታቸዉ ጀርመን አፍጋኒስታንን ከመርዳት ወደ ኋላ እንደማትል ለማሳየት ነዉ ሲሉም ገልጸዋል። ለጸጥታዉ ጥበቃ ሲባል የጀርመኑ ፕሪዝደንት አፍጋኒስታን መጎብኘታቸዉ በቅድሚያ አለመገለጹም ተጠቅሶአል። ጀርመን በአሁኑ ወቅት በአፍጋኒስታን ተሰማርቶ በሚገኘዉ አለማቀፉ የሰላም አስከባሪ ጦር (ISAF) ዉስጥ 5000 ያህል ወታደሮች አሏት።

አዜብ ታደሰ

መስፍን መኮንን