የዶይቼ ቬሌ ምርጥ የድረ ገጽ ጸሐፍት ሽልማት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 03.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የዶይቼ ቬሌ ምርጥ የድረ ገጽ ጸሐፍት ሽልማት

ዶይቼ ቬሌ ለምርጥ የድረ ገጽ ጸሐፍት የሚያዘጋጀዉ «ቦብ» የተባለው ሽልማት የ2016 ተሸላሚዎች ስም ይፋ ሆነ። ዘንድሮ የተመረጡት ተሸላሚዎች አራት ሲሆኑ፣ ለአንድ ዘጋቢ ፊልም ፣ ለአንድ አፕሊኬሽን ፣ ለአንድ የከያንያን ቡድን ዘመቻ እና ለአንድ የሴቶች መብት ተሟጋች ፕሮጀክት የተመደበው ሽልማት ከአንድ ወር ተኩል በኋላ ይሰጣል።

«ቦብ» የተባለው የዶይቼ ቬሌ ምርጥ የድረ ገጽ ጸሐፍት የ2016 ሽልማት አሸናፊዎቹን የመምረጡ ስራ ቀላል 14 ዳኞች ለተጠቃለሉበት ቡድን ቀላል አልነበረም። ለሽልማቱ ሊበቁ ይችሉ ይሆናል በሚል ከቀረቡላቸው 2300 ስሞች መካከል ዳኞቹ አራት ተሸላሚዎችን መርጠዋል። (https://thebobs.com/deutsch/:"Bobs )

በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በላኩዋቸው የተወዳዳሪዎች ዝርዝር ውስጥ የተለያዩ ድረ ገፆች፣ የኢንስታግራም አድራሻዎች፣ የስማርትፎን አፕሊከሸኖችን እና የፌስቡክ ገፆች ይገኙባቸዋል። ለዘንድሮው ሽልማት ለተፎካካሪነት የቀረቡት ፕሮጀክቶች በተለይ ያጎሉት የድረ ገጽ ጸሐፍቱ በጠቅላላ ሀሳብን በነፃ ለመግለጽ እና ለሰብዓዊ መብት ለመታገል በኢንተርኔት ምን ያህል የተለያየ አማራጭ እንዳላቸው ነው።
« ሲቲዘን ጀርናሊዝም» በሚለው ምድብ ስር ከተወዳደሩት መካከል «ሬይዘርስ ኤጅ» የተሰኘው የባንግላዴሽ ዘጋቢ ተንቀሳቃሽ ስዕል ተሸላሚ ሆኖዋል። ዘጋቢ ተንቀሳቃሽ ስዕል ባንግላዴሽ ውስጥ መንግሥትን የሚተቹ የድረ ገጽ ጸሐፍት እና ደራስያን ስራቸውን የሚያከናውኑበትን አደገኛ ሁኔታ ያሳያል። በድንበር የማይገድበው ዘጋቢዎች ድርጅት(«ሪፖርተርስ ዊዝአውት ቦርደርስ») ዘገባ መሰረት፣ እጎአ በ2015 ዓም በብዛት ሙስሊሞች በሚኖሩባት ባንግላዴሽ ሀይማኖትን ማዕከላይ ትኩረታቸው ያላደረጉ አራት የድረ ገጽ ጸሐፍት በተጣለባቸው ጥቃት ህይወታቸውን አጥተዋል። ለዘብተኛ የድረ ገጽ ጸሐፍት፣ አሳታሚዎች እና ምሁራንም የፅንፈኛ ሙስሊሞች ጥቃት ሰለባ ሆነዋል።
ስለ ፕሬስ እና ሃሳብን በነፃ ስለመግለጽ ነፃነት የሚተርከውን የ17 ደቂቃ ዘጋቢ ተንቀሳቃሽ ስዕል የሰራው በስደት የሚኖረው የባንግላዴሽ ተወላጅ ናስትኬር ዳርማካታ ሲሆን፣ ዩቲዩብ ላይ በጫነዉ «ሬይዘር ኤጅ» በተባለው ፊልም አማካኝነት ለመንግሥቱ በማይመቹ የድረ ገጽ ጸሐፍት ላይ በሚጣለው ጥቃት ቅንብር ላይ በከፍተኛ ስልጣን ላይ የሚገኙ የባንግላዴሽ ፖለቲከኞችም እጅ እንዳለበት ማሳየቱን ከ14 ዳኞች መካከል አንዷ የሆኑት ራፊዳ አህመድ ገልጸዋል።


« የአንድ ሀገር መንግሥት ወንጀል ሳይቀጣ የሚታለፍበትን አሰራር በሚያበረታታበት ጊዜ ፣ ያኔ የሀገሪቱ ዜጋ ፍትሕ እንዲሰጥ የመጠየቅ ኃላፊነት አለበት። እና ዘጋቢው ፊልምም ይህንኑ ነው ያደረገው። መንግሥት ይህንኑ ወንጀል ካለቅጣት የሚታለፍበትን አሰራር እያበረታታ መሆኑን ጥሩ በሆነ ዘዴ አሳይቶዋል። »
በቴክኒክ ምድብ ደግሞ «ጌርሻድ» የተሰኘዉ የኢራናውያን የስማርትፎን አፕሊኬሼን (https: //www.gershad.com/: Persian smartphone app) ተሸላሚ ሆኖዋል። ኢራን ዉስጥ ሴቶች አደባባይ ሲወጡ ሂጃብ መልበስ ይገደዳሉ። ይህን በተመለከተ በየመንገዶች እና በየአደባባዩ ሁሌ ቁጥጥር ይደረጋል፣ ሕጉን ያላከበረም ይቀጣል። «ክራዉድ ሶርስንግ ፕሪንስፕል» የሚለውን መመሪያ የሚከተለው የ«ጌርሻድ» አፒሊከሽንን ያስተዋወቁት ሰዎች፣ ተቆጣጣሪዎቹ የት እንዳሉ ሴቶች በዚሁ አፕሊኩሽን አማካኝነት መረጃ በመለዋወጥ አስቀድመው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አስችሏቸዋል። # # BbiG
ዳኞቹ «ቦብ» ወይም ምርጥ የድረ ገጽ ሽልማትን ለ«ጌርሻድ» አፒሊከሽን ለመስጠት የወሰኑበት ምክንያት ብዙ ሰዉን ስለሚጠቅም በመሆኑ መሆኑን የዳኞቹ ቡድን አባል የሆኑት ጎሊናዚ ኤስፋንዲራይ አስረድተዋል።
« ይህ አፕሊኬሽን ብዙ ሰዎችን ይረዳል። በሚልዮን የሚቆጠሩ ሴቶች እነዚህ ተቆጣጣሪዎች በሚደቅኑት እክል ችግር ያጋጥማቸዋል፣ ክትትል ያርፍባቸዋል ወይም ያስሩዋቸዋል። አፕሊኩሽኑ ከመረጃ ልውውጡ አገልግሎት ጎን፣ የኢራን መንግሥት ሴቶች ሂጃብ እንዲለብሱ ለማስገደድ የሚጠቀምበትን ጨቋኝ ርምጃ ያጎላል። እና ኢራናውያን ሌላ ምርጫ እንደሌላቸውም ያሳያል። »
በኪነት እና ባህል ምድብ ስር ደግሞ «ሴንቴር ፎር ፖለቲካል ቢውቲ» የተሰኘዉ ድረ ገጽ (www.politicalbeauty.de ) የዳኞቹን ቀልብ መሳብ ችለዋል። የተለያዩ ከያንያን በተለያዩ ዘዴዎች በሚያካሂዱዋቸው ዘመቻዎች ለምሳሌ በአውሮጳ ህብረት የስደት ፖሊሲ ወይም ጀርመን በንግድ ወደሳውዲ ዐረቢያ በምትልከው የጦር መሳሪያ አንፃር ተቃውሟቸውን ይገልጻሉ።
ማህበራዊ ለውጥ በሚለው ምድብ ስር ለዶይቼ ቬሌ ምርጥ የድረ ገጽ ጸሐፍት የቦብ ሽልማት ሽልማት የበቃው «ስቶፒ አስድ አታክ» በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ፊልም በተለይ በሴቶች ላይ በአሲድ የሚጣለውን ጥቃት ያወግዛል። (www.stopacidattacks.org )
(#link: https: //www.facebook.com/SheroesHangout)።
የአራቱ ምድቦች አሸናፊዎች ከሰኔ 13 እስከ ሰኔ 15፣ 2016 ዶይቼ ቬለ በቦን በሚካሄደዉ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን መድረክ ላይ ሽልማታቸውን እንደሚቀበሉ ተገልጾዋል።

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic