የዶይቸ ቬለ የ65 ዓመት ጉዞ  | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 03.05.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የዶይቸ ቬለ የ65 ዓመት ጉዞ 

«የተከበራችሁ የውጭ ሀገር አድማጮቻችን»በሚል የጀርመን ፕሬዚዳንት ቴዎዶር ሆይስ ባሰሙት ሀረግ ነበር ዶይቸ ቬለ በጎርጎሪዮሳዊው ግንቦት 3 ቀን፣ 1953 ዓ.ም ነበር ስርጭቱን የጀመረው፡፡ይህ ሬዲዮ ጣቢይ ሲመሰረት የጀርመንን ፖለቲካዊ ፤ ኤኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ገጽታዎችን ለውጭ ሀገር ታዳሚዎች ለማቅረብ ነበር፡፡

ዶይቸ ቬለ ሲመስረት በጀርመንኛ ቋንቋ ብቻ በውጭ ሀገር የሚደመጥ የአጭር ሞገድ ሬዲዮ ጣቢያ ነበር፡፡ በጎርጎሮሳውያኑ 1953 ዓ.ም ግን በሌሎች የውጭ ቋንቋዎች ማስተላለፍ ጀመረ፡፡ በ1992 ዓ.ም ደግሞ የቴሌቪዥን ስርጭት አድማሱን አሰፋ፡፡ ትንሽ ቆይቶም ወደ በይነ መረብ ስርጭት ተሸጋገረ፡፡«በእርግጥ አነዚያ የአጭር ሞገድ ስርጭት ጊዚያቶች አስቸጋሪ አልነበሩም»ይላሉ የዶይቸ ቬለ ዋና ስራ አስኪያጅ ፒተር ሉምበርግ ፡፡ ነገር ግን «ከበይነ-መረብ ፤ ለማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችና ሌሎች የትሥሥር መድረኮች ምስጋና ይግባቸውና አሁን ከበፊቱ በተሻለ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው መድረስ ዕድሉ አለን፡፡ ዜናዎቻችንን፣ ትንታኔዎቻችንን፤ ፕሮግራሞችን፤ሃሳቦችን ዘመናዊ በሆነ መንገድ በብዛሃነትና በወጣት ታዳሚዎቻችን ፍላጎት ላይ አትኩረን እናቀርባለን፡፡ »
ዶይቸ ቬለ ፤ በሬዲዮ ስርጭቱ ብዙ ተጉዟል፡፡አሁን በአራት ቋንቋዎች የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን ያሰራጫል፡፡ የተለያዩ የድምፅ ይዘቶችን ያቀርባል፡፡ በ 30ቋንቋዎች በበይነ-መረብ ዜናዎች ያሰራጫል፡፡ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችም ዘልቆ ገብቷል፡፡ ታዳሚውም እንደቀድሞው አይደለም ፡፡ ተለውጧል፡፡ ዛሬ ብዙ ሰዎች በእጅ ስልኮቻቸው ዜና ማግኘት ይችላሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት አድማጮች ተከታዮች ሆነዋል፡፡


በስልጠና በኩልም ዶይቸ ቬለ ከ1965 አ.ም ጀምሮ በማሰልጠኛ ጣቢያው በአለም ዙሪያ በሺህ የሚቆጠሩ ጋዜጠኞችን አሰልጥኗል፡፡የጀርመን ባለስልጣናትና ሚንስትሮች ወደ ውጭ ሀገራት ሲሄዱ ዶይቸ ቬለ እንዴት ተፅዕኖ ፈጥሮባቸው እንደነር የሚነግሯቸው ስዎች ብዙ ናቸው፡፡ 
ዶይቸ ቬለ አስቸጋሪ ጉዞዎች ተጉዟል፡፡ጣቢያው ከተመሰረተ በኋላ በነበሩት አምስትና ስድስት አመታት የዓለም ዓቀፉ የፖለቲካ ሁኔታ በብዙ ጉዳዮች ከ1953 አ.ም ተመሳሳይ ነበር፡፡የቀዝቃዛው ጦርነት ሰጋት መጨመር፤ የመፃፍና የመናገር ነፃነት በአብዛኛው የዓለም ክፍል አደጋ ላይ የወደቀበት ጊዜ ነበር፡፡«ጊዜው በጣም አስቸጋሪ ነበር፡፡ያ ማለት ለዶይቸ ቬለ ተጨማሪ ስራ ነበር፡፡» ሲሉ ነው፡፡ወቅቱን የገለፁት፡፡«መረጃ ማቅረብ እንፈልጋለን፡፡የተግባቦት ድልድዮችንና እሴቶችን መገንባት እንፈልጋለን፡፡አዲሱ የቀዝቃዛ ጦርነትም በሉት ወይም በዙ ጫፎች ያሉት የፖለቲካ ስርዓት ከፐሮፖጋንዳ፤ከሀስት ዜናዎች፤ከስደት፤ካአየር ንብረት ለውጥና ከሽብርተኝነት የሚመጣው ተግዳሮቶች እንዱጨምር አድርጓል፡፡»በዚህ ወቅት ዶይቸ ቬለ በቻይናና በአኢራን በከፊል ታግዶ ነበር፡፡ሁኔታው አሳዛኝ ቢሆንም «ስራችን በጣም ተገቢ ነው»የሚለውን የሊምቡርግ አባባል ያረጋግጣል፡፡በአሁኑ ወቅት ተቀናቃኝ የፖለቲካ ስረዓትና ርዕዮተ ዓለም የሚንፀባረቀው በዓለም ዓቀፍ የመገናኛ ብዙሃን መካከል በሚደረግ ውድድር ሆኗልና፡፡ 

ዶይቸ ቬለ በበርሊንና በቦን ማሰራጫ ጣቢያዎቹ ከ60 ሀገራት የሆኑ 3ሺሀ 4መቶ ሰራተኞች አሉት፡፡ይህ ጀርመንን የብዝሃ ባህል ማስራጫ ጣቢያ ባለቤት አድርጓታል፡፡በአፍሪካ ፤በእስያና በደቡብ አሜሪካ የርቀት ዘጋቢዎች ቁጥርም እየጨመረ መጥቷል፡፡ «ይህ ብዝሃነት ለዶቼ ቭለ ውድ ሀብትና አንዱ ጥንካሪያችን ነው፡፡» ይላሉ ሉምቡርግ፡፡አንዳችን ከአንዳችን እንማራለን፡፡የባህሎች ፡የሀይማኖቶችና የልማዶች መስተጋብር ፈጠራንና መሻሻልን ያመጣል፡፡እነዚህ ሁሉ በጀርመን ህገ-መንግስት ዲሞክራሲያዊ እሴቶች ላይ የተመስረቱ ናቸው፡፡«ለእኔ» ይላሉ ሊምቡርግ « ከተለያዩና ለሰራ ከሚያነሳሱ ባልደረቦች ጋር መስራት ትልቅ ደስታ ነው።»

ለመሆኑ ቀሪው ዓለም ስለ ዶይቸ ቬለ ምን ያስባል?

ሳንድራ ፒተርሰን ግጭት ባለባቸው ቀጠናዎች በመዘገብ ልምድ ያላት የዶይቸ ቬለ ነባር ጋዜጠኛ ነች፡፡በ 2000 ዓ.ም ወጣት ጋዜጠኛ እንደመሆኗ መጠን ከአንድ የእርዳታ ድርጅት ከሚስራ የሀኪሞች ቡድን ጋር በኤርትራ በኩል ወደ ምስራቅ አፍሪቃ ተጉዛ ነበር፡፡ገጠመኟን እንዲህ ነበር የገለፀችው፡፡
«አንድ ቀን ከስዓት በኋላ በአንዲት ትንሽ መንደር አለፍን፡፡በአንዲት በባትሪ በምትስራ ትንሽ ራዲዮ ዙሪያ በኮሶ ዛፍ ስር በርካታ ሰዎች ተሰባስበዋል፡፡ የጣቢያው መክፈቻ የዶይቸ ቬለ መሆኑን አውቂያለሁ፡፡ነገር ግን የአማርኛው ክፍል ባልደረቦቼ የሚሉትን አንድም ቃል አልገባኝም ነበር፡፡ነገር ግን ለሰዎቹ የዶይቸ ቬለ ባልደረባ እንደሆንኩ ራሴን ሳስተዋውቅ ወዲያውኑ ነበር ባህላዊውን የቡናና የእጣን ስነስርዓት የተጋ በዝኩት» ጋዜጠኛዋ ቴሌቪዥን በሌላቸና የመረጃ ረሀብ ባለባቸው የአፍጋኑስታን መንደሮችም ተመሳሳይ ገጠመኝ አላት፡፡እሷም ልክ እንደሊሎቹ የዶይቸ ቬለ ባልደረቦች በብዙ ቋንቋዎች የሬዲዮ ፕሮግራሞች መተላለፍ ባለመቀጠላቸው ትቆጫለች፡፡ነገር ግን ጊዜው ተለውጧል፡፡ፖድካስትና ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የጊዜው ቅመሞች 
በቱርክና በዮርዳኖስ በሚገኙ የስደተኛ ጣቢያዎች በዶይቸ ቬለ መነጋገሪያ ፊት ሲቀርቡ ታሪካቸውን ለመናገር ይጓጓሉ፡፡

ጃፋር አብዱል ከሪም በዶይቸ ቬለ የአረብ ኛው ክፍል በጣም የታወቀ ነው፡፡ወደ ቤሩት ፡ወደ ኦማን ወይም ወደ ካይሮ ከሄደ፤ወጣቶች ወደ እርሱ ይጎርፋሉ፡፡«ሸባብ ቶክ» የሚለው ፕሮግራሙ በብዙ የአረብ ሀገራት የመንግስት የቴሌዥን ጣቢያዎች የማይዳስ ሱትን ጉዳዮች ይዳስ ሳል፡፡ እናም ወጣት የፕሮግራሙ ተክታታዪች አንድ ሚሊዮን ደርሰዋል፡፡
በኡርዱ፡በፓሽቱና ብቻይና ቋንቋዎች በበይነ-መረብ የሚቀርቡ ፅሁፎች በ አስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች የከታተሉታል፡፡በተለይ ጉዳዩ ከመናገር ነፃነት፡ለሴቶች መብት፡ከሙስናና ከተሻለ የትምህርት ዕድል ላይ የሚያተኩር ከሆነ።
የመራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርከልን አስተዳደር ብዘመነ ዶናልድ ትራምፕና በዘመነ ብላድሚር ፑቲን የጀርመንን የመንግስት ፖሊሲሲዎች ባለሙያዎች ሲተነትኑ በአንፃሩ ሀገሪቱ ከዶይቸ ቬለ  ያገኘችውን ትርፍ ጀርመኖች ያደንቃሉ ነዉ ያሉት፡፡
የውጭ ሀገር የማስራጫ ጣቢያዎች ህልውና በተለይ « በዶይቸ ቬለ መመሪያ ደንብ»እና በጀርመን ምክር ቤት/ቡንደስታግ/ ዋስትና አለው፡፡ምክር ቤቱ የሀገሪቱን የዓለምቀፍ የመገናኛ ብዙሃን እድገትን በትኩረት ይከታተላል፡የህንን አስመልክቶ የሶሻል ዲሞክራቲከ መገናኛ ዘዴዎች ቃል አቀባይ ማርቲን ራባኑስ «ይህ ተቋም እውነታዎችን እንጅ የሀስት ዘገባዎችን ማቅረብ የለበትም።» ሲሉ በቅርቡ ለምክር ቤቱ የገለፁት፡፡«ተቋሙ ነፃ ፤ፈጠራ ያለው፤በእሴት የተገነባና ስሜት ያለው ነው»ሲሉ ቃል አቀባዩ አክለዋል፡፡
ዶይቸ ቬለ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በተሰበሰበ ድምፅ 96 የሚሆኑት ታዳሚዊቹ ጣቢያው ተአማነት እንዳለው ገልፀዋል፡፡ያ ማለት በሳምንት ከ150 ሚሊዮን በላይ ስዎች ማለት ነው፡፡በሚያስገርም ሁኔታ እያደገ ያለ ቁጥር፡፡

ጄፈርሰን ቼይዝ/ፀሐይ ጫኔ

አርያም ተክሌ