የዶክተር ዐብይ የአንድ ዓመት የሥልጣን ዘመን | ኢትዮጵያ | DW | 01.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የዶክተር ዐብይ የአንድ ዓመት የሥልጣን ዘመን

በሥልጣን ዘመናቸው በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ተፈተዋል፤ ቁም ስቅል ይፈጸምባቸው የነበሩ እስር ቤቶች ተዘግተዋል፣ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰላም አውርደዋል። ከኢትዮጵያ ካቢኔ ግማሹ በሴቶች እንዲያዝ ተደርጓል። በሌላ በኩል ባለፈው አንድ ዓመት በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰቱ ደም አፋሳሽ ግጭቶች የበርካታ ሰዎች ህይወት ጠፍቷል፣ ብዙዎች ተፈናቅለዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 31:14

የዶክተር ዐብይ የሥልጣን ዘመን

ዶክተር ዐብይ አህመድ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ቃለ መሀላ ፈጽመው በይፋ ሥልጣን ከተረከቡ የፊታችን ማክሰኞ አንድ ዓመት ይሆናቸዋል። ሥልጣን ከያዙ ወዲህም ኢትዮጵያ በለውጥ ሂደት ላይ ናት። በርሳቸው የሥልጣን ዘመን ለዓመታት በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ተፈተዋል፤ ቁም ስቅል ይፈጸምባቸው የነበሩ እስር ቤቶች ተዘግተዋል፣ በሽብርተኝነት ተፈርጀው የቆዩ በውጭ ሀገራት የሚገኙ ልዩ ልዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገራቸው ገብተው እየተንቀሳቀሱ ነው።   ለዓመትት በጠላትነት ሲተያዩ የበሩት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በመካከላቸው ሰላም አውርደዋል። አፋኝ እና የማያንቀሳቅሱ የሚባሉ የተለያዩ የሀገሪቱ ህጎች ማሻሻያ እየተደረገባቸው ነው። የተሻሻሉ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽድቅያን የሚጠብቁም አሉ ። ባለፈው አስተዳደር በሙስና የተጠረጠሩ የቀድሞ ባለሥልጣናት ለፍርድ ቀርበዋል። ከቀድሞው በተለየ ከኢትዮጵያ ካቢኔ ግማሹ በሴቶች እንዲያዝ ተደርጓል። ሀገሬቱ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰየምላት ፣ በሌሎች ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎችም ሴቶች ተሹመዋል።በሌላ በኩል ባለፈው አንድ ዓመት በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰቱ ደም አፋሳሽ ግጭቶች የበርካታ ሰዎች ህይወት ጠፍቷል፣ ብዙዎች

ተፈናቅለዋል። ንብረት ወድሟል። ባንኮች የተዘረፉባቸው የሰዎች እንቅስቃሴ የተገደበባቸው፣ትምሕርት የተስተጓጎለባቸው አካባቢዎችም አሉ። ከቀድሞው አሁን የደህንነት ስጋት ያየለባቸው አካባቢዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ይነገራል። እነዚህ ከሞላ ጎደል ያለፈው አንድ ዓመት የኢትዮጵያ አዎንታዊ እና አሉታዊ ገጽታዎች ናቸው። የዛሬው እንወያይ የዶክተር ዐብይ አህመድን የአንድ ዓመት የሥልጣን ዘመን ስኬት፣ ተግዳሮትና የወደፊቱን ተስፋ ይቃኛል። በዚህ ውይይት  አቶ ተማም አባቡልጎ ጠበቃ እና የህግ ባለሞያ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ዳንኤል መኮንን በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር እንዲሁም አቶ ሞኔኑስ ሁንደራ የፌደራሊዝም እና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ተሳትፈዋል።ሙሉውን ውይይት ለመከታተል የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። 

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

 

Audios and videos on the topic