የዶክተር መረራ የዋስትና ጥያቄ ይግባኝ ጉዳይ | አፍሪቃ | DW | 07.04.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የዶክተር መረራ የዋስትና ጥያቄ ይግባኝ ጉዳይ

ዶክተር መረራ ለችሎቱ ሰላማዊ ታጋይ መሆናቸውን አስታውቀው በፖለቲካ ምክንያት መታሰሬ ይታወቅ ሲሉ ተናግረዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:36

የዶክተር መረራ የዋስትና ጥያቄ ጉዳይ

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዶክተር መረራ ጉዲና ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ይግባኝ ዛሬ ተመለከተ ። ዛሬ ከሰዓት በኋላ ጉዳዩን የተመለከተው ይኽው ችሎት ጉዳዩን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ህግ ተላልፈዋል ተብለው የተከሰሱት ዶክተር መረራ ለችሎቱ ሰላማዊ ታጋይ መሆናቸውን አስታውቀው በፖለቲካ ምክንያት መታሰሬ ይታወቅ ሲሉ ተናግረዋል ። በሌላ በኩል የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ነኛ ወንጀል ችሎት በበኩሉ በእነ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ ጆሀር መሐመድ የተመሰረተው ክስ በሌሉበት እንዲታይ መበየኑን  የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘግቧል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ 

Audios and videos on the topic