የዶክተር መረራ ክስ ሒደት | ኢትዮጵያ | DW | 01.08.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የዶክተር መረራ ክስ ሒደት

ችሎቱ ከዚሕ ቀደም የሕግ ትርጓሜ እንዲሰጥበት ለኢትዮጵያ ፌደሬሽን ምክር ቤት የላከዉ ማስረጃ እስካሁን ድረስ ከምክር ቤቱ እንዳልደረሰዉ አስታዉቃል። ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት ለጥቅምት ስድስት ቀን 2010 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:19

የዶክተር መረራ ክስ ሒደት

በተለያዩ የወንጀል ጭብጦች ተከሰዉ የታሠሩት የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚ ፓርቲ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) የቀድሞ ሊቀመንበር የዶክተር መረራ ጠበቃ ደንበኛቸዉን መጎብኘትና ማነጋገር እንዲችሉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ አዘዘ። ችሎቱ ከዚሕ ቀደም የሕግ ትርጓሜ እንዲሰጥበት ለኢትዮጵያ ፌደሬሽን ምክር ቤት የላከዉ ማስረጃ እስካሁን ድረስ ከምክር ቤቱ እንዳልደረሰዉ አስታዉቃል። የተከሳሽ ጠበቃ እንዳሉት ፍርድ ቤቱ በትርጓሜ ሰበብ የፍርድ ሒደቱን ማጓተቱ ተከሳሾን እየጎዳ ነዉ። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic