የዶቸ ቨለ ዘጋቢዎችና የሙያ ማሻሻያው ሥልጠና፣ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 26.11.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የዶቸ ቨለ ዘጋቢዎችና የሙያ ማሻሻያው ሥልጠና፣

በ 32 የተለያዩ ቋንቋዎች በዓለም ዙሪያ ፕሮግራሞችን የሚያሠራጨው ዶቸ ቨለ ራዲዮ ጣቢያ፣ ቋሚ ሠራተኞቹ ብቻ ሳይሆኑ፣ በተለያዩ አገሮች የሚገኙ ዘጋቢዎቹም በየጊዜው ሙያዊ ማሠልጠኛ እንዲያገኙ ያደርጋል።

የዶቸ ቨለ ዘጋቢዎችና የሙያ ማሻሻያው ሥልጠና፣

በመሆኑም፣ ባለፉት ሁለት ሳምንታት፣ በተሰጠው የሙያ ማሻሻያ ኮርስ ከተካፈሉት መካከል ከጂዳ ፣ ስዑዲ ዐረቢያና ከአሥመራ፣ ኤርትራ የመጡት የዶቸ ቨለ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢዎች ፣ ነቢዩ ሲራክና ጎይቶም ቢሆን ይገኙበታል። ሥልጠናውን ፤ የቱን ያህል ጠቃሚ ሆኖ እንዳገኙት ተክሌ የኋላ አነጋግሮአቸዋል።

ዛሬ የሁለት ሳምንቱ ሥልጠና የተደመደመ ሲሆን ፣ ሁለቱም የሩቅ ባልደረቦቻችን በእርካታ መንፈስ ነበረ ወደ እስቱዲያአችን ብቅ ብለው ያጫወቱን። በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ በራይን ወንዝ አካባቢ የጣለውና በየመንገዱ፤ በየመስኩና በየጥሻው የተቆለለውን በረዶ በመስኮት በኩል በማየት እያደነቁም ነው፤ ስለቀሰሙት የሙያ ማሻሻያ ትምህርት የነገሩን ። ነቢዩ ሲራክ፣--

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ