የዶርዜ የማንነት ጥያቄ | ኢትዮጵያ | DW | 07.04.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የዶርዜ የማንነት ጥያቄ

በኢትዮጵያ የማንነት ጥያቄዎችን የሚያነሱ ብሄረሰቦች እየተበራከቱ ነዉ። ከእነዚህ መካከልም የዶርዜ ብሄረሰብ አንዱ ነዉ። በርካታ የማሕበረሰቡ አባላት በተገኙነት ሰሞኑን ሕዝባዊ ስብሰባ በማካሄድም ዶርዜ ከሌሎች የሚለይባቸዉን ነጥቦች በመዘርዘር ማኅበረሰቡ ከጋሞ ብሄር እንደሚለይ አመልክቷል።

የጉዳዩ አስተባባሪዎች የብሄረሰቦች መብት በተከበረባት ሀገር የዶርዜ ብሄረሰብ ተጨፍልቋል ባይ ናቸዉ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እንዲህ ያለዉን ጥያቄ ያቀረበዉ ዶርዜ ብቻ ሳይሆን ወደ13 የሚደርሱ ብሄረሰቦች መሆናቸዉን ያመለክታሉ። የማንነት እዉቅና ጥያቄ የሚቀርብለት ጉዳዩ የሚመለከተዉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ካሣ ተክለብርሃን እንደሚሉት ጥያቄዉ ቢቀርብም ምላሹን ለመስጠት ጥናትና ጊዜ ይጠይቃል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic