የድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት RSF ነቀፌታ | አፍሪቃ | DW | 04.01.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት RSF ነቀፌታ

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ላይ ትናንት ያሳለፈውን የጥፋተኝነት ብይን ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት በእንግሊዘኛው ምህፃር RSF ነቀፈ ።


የድርጅቱ የአፍሪቃ የአፍሪቃ ክፍል ሃላፊ Ambroise Piere ዛሬ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ሁለቱ ጋዜጠኞች አሸባሪነትን በመደገፍ መከሳሰቸውና ጥፋተኛ ናቸው ተብሎ መበየኑ ትርጉም እንደማይሰጥ ተናግረዋል ። ትናንት በተላለፈባቸው ውሳኔ መሰረትም ጋዜጠኞቹ ሊጠብቃቸው የሚችለው ብይን ድርጅታቸውን በእጅጉ እንደሚያሳስበውም አስታውቀዋል ። በዚህና በኢትዮጵያ የፕሬስ ይዞታ ላይ በማተኮር ዛሬ ፓሪስ ውስጥ በፈረንሳይ የኢትዮጵያው አምባሳደር ጋር መነጋገራቸውንም ገልፀዋል ። ያነጋገረቻቸው ሂሩት መለሰ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች
መቀመጫውን ፓሪስ ፈረንሳይ ያደረገው ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት በስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች ላይ ትናንት የተሰጠው ብይን አስቆጥቶታል ። ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛ ዮሀን ፔርሰንና እና ማርቲን ሽቤን ሽብርተኝነትን በመደገፍ ወንጀል ጥፋተኛ ናቸው ሲል ያስተላለፈውን  ብይን የድርጅቱ የአፍሪቃ ክፍል ሃላፊ Ambroise Piere ክፉኛ ነቅፈዋል ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋየ ለገሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 04.01.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/13Xwy
 • ቀን 04.01.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/13Xwy