የድሬ ቱይብ መስራች ቢኒያም ነገሱ | ባህል | DW | 18.07.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

የድሬ ቱይብ መስራች ቢኒያም ነገሱ

በተማሩት የቀለም ትምህርት ላይ የየግላቸዉ ጥረት አክለዉ ለስኬት የሚደርሱ ጥቂት አይደሉም። የዕለቱ የወጣቶች ዓለም እንግዳ ከእነዚህ አንዱ ነዉ።

ድሬ ቱይብ ዛሬ ትልቅ የመረጃ ማጠራቀሚያ ገፅ ሆኗል። የፌስ ኩክ ገፁ ወደ 617 ሺ ተከታዮች አሉት። እንዲሁም ዘውትር በሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ዋና ገፁን ይጎበኛሉ። የድሬ ቱይብ መስራች እና ባለቤት ቢኒያም ነገሱ የተማረው ትምህርት ከዛሬው ስራው ጋር ቢገናኝም አብዛኛውን ነገር ግን ራሱን በራሱ እንዳስተማረ ይናገራል።

ቢኒያም ለስራ ወደ ሶማሌላንድ እንዲያስተምር በሄደበት ጊዜም በውጭው ሀገራት የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ የተለያዩ መረጃዎች በአንዴ የሚያገኝበት አንድ ድረ ገፅ ለምን አይኖረንም በሚል ሀሳብ እንደተነሳሳ ይናገራል። ከስድስት አመት ገደማ በፊት ድሬ ቱይቡን የመሰረተው ቢኒያም ዛሬ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም 19 ኢትዮጵያውያን የስራ እድል መፍጠር ችሏል።

ድሬ ቱይብ ምን አይነት መስፈርቶችን ተጠቅሞ ነው የመረጃዎችን ይዘት የሚገመግመው እና ለተጠቃሚዎች የሚያቀርበው? ድሬ ቱይብ በገንዘብ ሲተመን ምን ያህል ነው? ለዚህ እና ሌሎች ጥያቄዎች ቢንያም የሰጠንን ምላሽ ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic