የድሬዳዋ ዛፎችና ወጣቱ | ኢትዮጵያ | DW | 16.08.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የድሬዳዋ ዛፎችና ወጣቱ

የድሬዳዋዉ ወጣት ዋለለኝ መኮንን በእሱ ጉልበት፥ አቅምና እዉቀት ይደረጋል ተብሎ የማይገመት ምግባር እያካናወነ ነዉ።

default

ዋለልኝ፥-የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ እንጂ-የከተማይቱ ማዘጋጃበት አይደለም።ግን የከተማይቱ ማዘጋጃበት ያልሠራዉን፥ ሊሰራዉ ያልፈለገዉን ወይም ለመስራት ያቃተዉን ወጣቱ ብቻዉን እየሠራ ነዉ።ዋለልኝ እኒያን የድሬዳዋ ዉበት፥ መለያና መታዋቂያ የሆኑን አንጋፋ ዛፎች ለመንከባከብ፥ ጊዜ፥ ጉልበትና ትንሽ ጥሪቱን በሙሉ ለነሱዉ አዉሏል።ዛፎቹ በእንክብካቤ እጦትና በእድሜ መገርጀፍ መክንያት እየተሰባበሩና እየወደቁ ነዉ።የወደፊቱ እይታወቅም ላሁኑ ግን የድሬዳዋዉ ወኪላችን ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር እንደዘገበዉ ዋለልኝ ዋለላቸዉ።

ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሀመድ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic