የድሬደዋ፤ ሀረር፤ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ  | ኢትዮጵያ | DW | 28.10.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የድሬደዋ፤ ሀረር፤ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ 

በድሬደዋ ከሦስት ቀናት በፊት ጀምሮ ነግሶ የነበረዉ ከፍተኛ ስጋትና ዛሬ ረገብ ማለቱ ተገለፀ። በሀረር ፤ምዕራብና ምስራቅ ሃረርጌ ያለዉ የፀጥታ ሁኔታ ከድሪደዋ በተሻለ መልኩ ሰላማዊ መሆኑ ተመልክቶአል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:50

ሥጋቱ በጥቂቱም ቢሆን በረድ ብሎአል

በድሬደዋ ከሦስት ቀናት በፊት ጀምሮ ነግሶ የነበረዉ ከፍተኛ ስጋትና ዛሬ ረገብ ማለቱ ተገለፀ። በሀረር ፤ምዕራብና ምስራቅ ሃረርጌ ያለዉ የፀጥታ ሁኔታ ከድሪደዋ በተሻለ መልኩ ሰላማዊ መሆኑ ተመልክቶአል። የድሬደዋዉ ወኪላችን መሳይ ተክሉ በስልክ እንደገለፀልን ከሆነ በድሬደዋ ሃይማኖታዊ መልክ የያዘ የሚመስለዉ ውጥረት የመከላከያ ሰራዊት ስፍራዉ ላይ ከገባ በኋላ በጥቂቱም ቢሆን የተሻለ መስሎአል። ማኅበረሰቡም የቤተ እምነቱን እራሱ እየጠበቀ ነዉ። በማኅበራዊ መገናኛዎች በሚሰራጨዉ የተለያየ ዉዥንብር ምክንያት ግን እስካሁን ትምህርት ቤቶች በሮቻቸዉን ለተማሪዎቻቸዉ መክፈት የቻሉ አይመስልም ተብሎአል።  የንግድ ተቋማትም ቢሆኑ ሙሉ በሙሉ ስራ ጀመሩ ማለት አይቻልም።

 
መሳይ ተክሉ

 
አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ 
 

Audios and videos on the topic