የድሬስደኑ ዕልቂት ሲታወስ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 27.02.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የድሬስደኑ ዕልቂት ሲታወስ

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የተባበሩት ኃይሎች ባካሄዱት የቦምብ ድብደባ ከፍተኛ የህይወትና የንብረት ጥፋት ከደረሰባቸው የጀርመን ከተሞች ውስጥ ድሬስደን የተባለችው የምስራቅ ጀርመንዋ ከተመ ትገኝበታለች ።

default

ድሬስደን ከጦርነቱ በፊትና በኃላ

እ.አ.አ የካቲት አስራ ሶሶት ለየካቲት አስራ አራት አጥቢያ ይህች ከተማ በተደበደበች ወቅት በርካታ ህዝብ የተፈጀ ሲሆን ከተማይቱም እንዳልነበረች ሆናለች ። ድሬስደን በቦምብ የጋየችበት ይህ ለሊት በከተማይቱ ህዝብ ዘንድ በየዓመቱ ይታሰባል ። ይሁንና የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ በዚህ የመታሰቢያ ዕለት ወደ ከተማይቱ የሚመጡ ያልተጋበዙ ዕንግዶች የህዝቡን ስሜት እየረበሹ ነው ።