የድረ ገፆች ነፃነት መቀነስ | ዓለም | DW | 28.09.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የድረ ገፆች ነፃነት መቀነስ

በአፍሪቃ ጥናት ከተካሄደባቸው ሃገራት ውስጥ ኢትዮጵያ በድረገጾች ነፃነት የመጨረሻውን ደረጃ እንደምትይዝ ከአለም ደግሞ ከ6ቱ የመጨረሻ ሃገራት ውስጥ እንደምትገኝ ጥናቱ ጠቁሟል ።


በ47 አገራት የተካሄደ አንድ ጥናት በአለማችን የድረ ገፆች ነፃነት እያሽቆለቆለ መሆኑን ጠቆመ ። መቀመጫውን ዋሽንንግተን ዲሲ ያደረገው ፍሪደም ሃውስ የተባለው ተቋም ይፋ ባደረገው ጥናት እንደገለፀው አምባገነኖች የድረ ገፆችን ነፃነት ለመገደብ የተለያዩ የመቆጣጠሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም ላይ ናቸው ። በአፍሪቃ ጥናት ከተካሄደባቸው ሃገራት ውስጥ ኢትዮጵያ በድረገጾች ነፃነት የመጨረሻውን ደረጃ እንደምትይዝ ከአለም ደግሞ ከ6ቱ የመጨረሻ ሃገራት ውስጥ እንደምትገኝ ጥናቱ ጠቁሟል ። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ልኮልናል ።
አበበ ፈለቀ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic