የድረ-ገፅ አገልግሎትና ትምሕርት | ዓለም | DW | 17.03.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የድረ-ገፅ አገልግሎትና ትምሕርት

የዚሕ አይነቱ ትምሕርት ትልቅ አሉታዊ ጎንም አለዉ።ቴክኒካዊ ችግር አንዱ ፈተና ነዉ።አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ሐይልና የጠራና የማይቋረጥ የሥልክ መስመር መኖር ግድ ነዉ

default

«ዲጂታል» የተሰኘዉ የኮፒዉተር አገልግሎት ለትምሕርት መስጪያነት ከዋለ ጥቂት አመታት አስቆጥሯል።ባለሙያዎች እንደሚሉት በኮምፒዉተርና በኢንተርኔት (ድረ-ገፅ) የሚሰጠዉ ትምሕርትና የሚደረገዉ የእዉቀት ልዉዉጥ ወደፊት ይበልጥ መስማፋፋት፥ መጠናከርም አልለበት።ይሕ የባለሙያዎች እምነት የትምሕርትና የሥልጠናን ሒደት ቀላልና «ዴሞክራሲያዊ» ያደርገዋል ማለት ነዉ? የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ ነዉ።ገቢራዊነቱ ግን ዳንኤላ ዚበርት እንደዘገበችዉ ቀላል አይደለም።የዚበርትን ዘገባ ነጋሽ መሐመድ አጠናቅሮታል።
«ከዲጅታል የመገለል ችግር ያጋጥማል።ከዚሕ በተጨማሪ የዲጅታል ማይምነት ችግርም አለ።ይሕ በጣም ትልቅ ጉዳይ ነዉ ብዬ አምናለሁ።,መልሱ ግን የመለገለል አደጋ አለ የሚል ሊሆን አይገባም።ሁል ጊዜም በሚከሰቱ እንቅስቃሴዎች መገለል ያጋጥማልና።እንደሚመሰለኝ ሁሉም የሚካተትበትን መንገድ መፈለግ ነዉ።»

ይላሉ ግርሐም አትዌል።ብሪታንያዊ ናቸዉ።የመስኩ ባለሙያ።የኮፒዉተሩን የርቀት ትምሕርት ኢ-ለርኒንግ ይሉታል-እነሱ።-ባጭሩ።ትምሕርት መስጠቱ ብዙዎቹ ባለሙያዎች እንደሚስማሙበት አይገድም።ግን ችግርም አለዉ ነዉ-የትዌል-መልዕክት።

ትምሕርቱን በቋሚነት ለመስጠት ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች የማይከፈልበት ፈጣን ሽቦ-አልባ የአካባቢያዊ መረብ-WLAN ሊኖራቸዉ ይገባል።ከተሞችም ይሕን የነፃ መስመር ማዘጋጀት አለባቸዉ።በብሬመን-ጀርመን ዩኒቨርስቲ በተጋባዥ መምሕርነት የሚሰሩ አንድ ፕሮፌሰር የኮሚፒዉ ተሩን የርቀት ትምሕርት ከመዝጋት ይልቅ ግልፅ አድርጎ የእዉቀት ልዉዉጡን ማለማመዱ ጠቃሚ ነዉ-ባይናቸዉ።ምክንያቱም ይሕ የርቀት ትምሕርቱ መደበኛዉን ትምሕርት የሚቀይር ሳይሆን የሚያሻሻል ነዉና።

ብሪታንያዊቷ የላስተር ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ጊሊ ሳልሞን በአዲሱ ቴክኖሎጂ የሚሰጠዉ ትምሕርት ልዩ ባለሙያ ናቸዉ።እሳቸዉ እንደሚሉት የዘመኑ ወጣት ሥለ ኮምፒዉተር ያለዉ እዉቀት ትምሕርቱን ለመከታተል የሚያስችለዉ ነዉ።የሚያስተምሩበት ዩኒቨርስቲያም በርቀት ትምሕርት ሰፊ ልምድ እንዳለዉ ፕሮፌሰርዪቱ አስታዉቀዋል።

«በላስተር ዩኒቨርስቲ ሰባት ሺሕ የርቀት ትምሕርት ተማሪዎች አሉ።አብዛኞቹ የሚከታተሉት የማስተርስ ኮርሶችን ነዉ።እነዚሕ ተማሪዎች በሙሉ ከታላቅዋ ብሪታንያ በራቁ ሐገራት በተለይ በመካከለኛዉና በሩቅ ምሥራቅ፥ በካረቢክ እና በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ ናቸዉ።ተማሪዎቹ በሙሉ ከገንዘብና መሳሪያቸዉ በተጨማሪ ሙሉ በሙሉ የመማር ድባብ ባለበት በቡድን የመማር እድልም አላቸዉ።ለምሳሌ የሥነ-ቅሬት ተማሪዎቻችን ሥለ ጥንቱ ማሕበረሰብ ያጠናቀርነዉን በሁለተኛ ዘመን ተገናኝተዉ ይማሩታል።»

ይሕ በኮፒዉተሩ የርቀት ትምሕርት አዲስ ሥልት ነዉ።ሰዎች በክፍል ደረጃ ሲታይ አንዳቸዉ ከሌላቸዉ በጣም የራቀ ሥፍራ ቢኖሩም በጋራ መማር ይችላሉ።ያም ሆኖ የዚሕ አይነቱ ትምሕርት ትልቅ አሉታዊ ጎንም አለዉ።ቴክኒካዊ ችግር አንዱ ፈተና ነዉ።አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ሐይልና የጠራና የማይቋረጥ የሥልክ መስመር መኖር ግድ ነዉ።

የትምሕርቱን አሰጣጥ ዘላቂነትና ጥራቱን የሚጠራጠሩና የሚተቹ ወገኖች እንዲሕ አይነቶቹ ችግሮች በብዙዎቹ ሐገራት ሳይቃለሉ የኮሚተር የርቀት ትምሕርት ጠቃሚና አስፈላጊ ነዉ መባሉን ያጣጥሉታል።ፕሮፌሰር ሳልሞን ግን ይሕን አይቀበሉትም።የኮሎኝ ከፍተኛ ኮሌጅ መምሕር ሚሻኤል ቲግሕም የተቺዎቹን አስተያየት በተለይም የኮፒዉተሩ ቴክኒካዊ ችግር ለትምሕርቱ አሰጣት እንደ ትልቅ እንቅፋት መቅረቡን ይቃወሙታል።

«ተማሪዎቹ በጣም የተካኑ ናቸዉ።አስገዳጅ ነገር ከመጣ እራሳቸዉ መፍትሔ ይሻሉ።ሁሉም የፌስ ቡክ ዘመን ትዉልዶች እና ናቸዉ።ኮምፒዉተር ሲበላሽ መትፍትሔ ወይም ተለዋጭ ለማግኘት በአንፃራዊ መመዘኛ ፈጣኖች ናቸዉ።»

ቲግሕ ለሚከራከሩለት ሐሳብ ጥሩ ገጠመኝም አላቸዉ።ባንድ ወቅት ቻይና የተማሪዎቻቸዉን የኢንተርኔት መስመር ትዘጋዋለች።ተማሪዎቸዉ የቻይና ባልጀሮቻቸዉ የጋጠማቸዉን ችግር ለማስወገድ ፈጥነዉ ተንቀሳቀሱ።መፍትሔም አገኙ ይላሉ መምሕሩ።

በየዲጅታሉ ዘመን የሰወዎች-ለሰዎች ግንኙነት እየተቀየረ፥ የዘመኑ ተማሪ-አስተማሪዎችም ነባሩን የገፅ-ለገፅ የትምሕርት ሒደት እየለወጡት ነዉ።ይሕ አዲስ እድል ነዉ።እና እድሉ ካለና በትክክል ከተጠቀሙበት ትምሕርቱ ተለዋዋጭ፥ ቀላልና «ዲሞክራሲያዊ» ይሆናል።

Daniela Siebert
ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic