የድረ ገፅ አምደኞች ሽልማት | ዓለም | DW | 03.05.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የድረ ገፅ አምደኞች ሽልማት

በዩኤስ አሜሪካ የሚኖረው ኢራናዊው የመንግሥት ተቃዋሚ አራሽ ሲጋርቺ ዶይቸ ቬለ እጅግ ምርጥ ለሚላቸው የድረ ገፅ አምደኞች በያመቱ የሚሰጠው ሽልማት አሸናፊ መሆኑን ዶይቸ ቬለ ዛሬ አስታወቀ። ዶይቸ ቬለ በኢንተርኔት ላካሄደው የዘንድሮው የድረ ገፅ አምደኞች ውድድር 187 የተሻሻለ እና ጥራት ያላቸው አምደ መረቦች በተፎካካሪነት ቀርበው ነበር።

ከዚያም የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች እአአ ካለፈው ሚያዝያ ሁለት እስከ ዛሬ ግንቦት ሁለት ድረስ በሰጡት ድምፅ የድረ ገፅ አምደኛውን አራሽ ሲርጋቺን ለአሸናፊነት መርጠዋል።

ጋዜጠኛው ሲጋርቺ አንድ ከፍተኛ የኢራን ዲፕሎማት በብራዚል አንዲት ወጣት ልጅ በወሲብ መድፈራቸው ለእሥላማሚው የኢራን ሬፓብሊክ እጅግ አሳፋሪ ነው በሚል በድረ ገፅ አምዱ ጽፎዋል። የምዕራቡ መገናኛ ብዙኃን ስለዚሁ ጉዳይ ሀቁን ፍርጥርጥ አድርጎ ነው ያቀረበው። የኢራን ኤምባሲ ግን ድርጊቱን ባህላዊ አለመግባባት ነው ብሎ አቃሎ ለማለፍ ነው የሞከረው። የኢራን መንግሥት የሀይማኖት ደንቦችን እንደሚከተል መናገሩን ሲጋርቺ በመግለጽ፡ ከትዳር ውጭ፡ ከዛ ባለፈም ለአካለ መጠን ካልደረሰች ወጣት ጋ የሚደረግ ግንኙነት እንደ ኃጢአትና ወንጀል እንደሚቆጠር አስታውቋል።

በኢራን መገናኛ ብዙኃን ቦታ የማያገኙ እዚህን የመሰሉ ዘገባዎች በስደት በዋሽንግተን የሚኖረው ሲጋርቺ እአአ ከ 2008 ዓም ወዲህ በኢንተርኔት በከፈተውና « የፍርሀት መስኮት » ብሎ በጠራው የድረ ገፅ አምዱ ይቀርባሉ። ሲጋርቺ በከፍተኛው የሀገሪቱ መሪ አሊ ኻሜኔይ ላይ በሰነዘራቸው ሂስ አከል አስተያየት የተነሳ ከአራት ዓመት በፊት በኢራን የአሥራ አራት ዓመት እሥራት ተፈርዶበት ነበር።
እርግጥ፡ በጠበቃው የኖቤል ሰላም ተሸላሚ ሽሪን ኤባዲ ርዳታ ቅጣቱ ወደ ሦስት ዓመት ዝቅ እንደለለትና በገጠመው የነቀርሳ በሽታ ከቅጣቱ መካከል አሥራ አራት ወር በወህኒ ማሳለፉ ይታወቃል። እዚያው እሥር ቤት እያለም ታናሽ ወንድሙ አሽካን በመኪና አደጋ ሕይወቱን ያጣል፤ ያም ቢህን ግን፡ ትግሉን አለማቋረጡን ዶይቸ ቬለ እጅግ ምርጥ ለሚላቸው የድረ ገፅ አምደኞች በያመቱ የሚሰጠው ሽልማትን የሚያገኘውን አምደኛ የሚመርጠው ቡድን አባል የሆኑት ኢራናዊው አራሽ አባድፑር አስታውቀዋል።
የአሥራ አምስት ዓመት ተሞክሮ ያለው ሲርጋቺ በሰሜን ኢራን የተወለደውና የአንድ ያካባቢ ጋዜጠኛ እና በኋላም ላይ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሰርቶዋል። ግን በሀገሪቱ በሚሰራበት ሳንሱር ወሳኝ ሆነው ስላገኛቸው መንግሥት የሚፈጽመው የሰብዓዊ መብት ረገጣን ስለመሳሰሉ ጉዳዮች መጻፍ ሳይችል ሲቀር ያኔ « የፍርሀት መስኮት » ብሎ የጠራውን የድረ ገፅ አምዱ መክፈቱን ይናገራል።
በእሥር ቤት እያለ ዶይቸ ቬለ እጅግ ምርጥ ለሚላቸው የድረ ገፅ አምደኞች በያመቱ የሚሰጠው ሽልማት ሂደትን መከታተሉን የገለጸው ሲርጋቺ ከድረ ገፁ አምዱ ጎን አሁን በዋሽንግተን ለቪኦኤ ይሰራል።
ዶይቸ ቬለ እጅግ ምርጥ ለሚላቸው የድረ ገፅ አምደኞች በያመቱ የሚሰጠውን ሽልማት አሸናፊ የሚመርጠው 12 አባላት ያሉት ዓለም አቀፍ የዳኞች ቡድን በበርሊን ሲርጋቺን ለዚህ ታዋቂ ሽልማት የዘንድሮ አሸናፊ አድርጎ መምረጡን በፍጹም ያልጠበቀው እንደነበር ቢያስታውቅም ተሸላሚ በመሆኑ ከፍተኛ ደስታና ኩራት እንደተሰማው ገልጾዋል። ዶይቸ ቬለ ሽልማቱን እአአ በ 2004 ዓም ያስተዋወቀው ሽልማቱ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳርፈውን በድረ ገፅ አስተያየት በነፃ የመሰንዘርና በግልጽ የመወያየትን ሂደት ለማራመድ ነበር።

ዶይቸ ቤለ እጅግ ምርጥ ለሚላቸው የድረ ገፅ አምደኞች በያመቱ የሚሰጠው ሽልማት የሚያስገኘውን ጥቅምን አስመልክተው የዶይቸ ቬለ የፕሮግራም ኃላፊ ወይዘሮ ኡተ ሼፈር እንዳስረዱት፡ ዶይቸ ቬለ በተለያዩ የዓለም አካባቢዎች ባካሄደው ውድድር መልካም ስም አትርፎዋል። እና የዘንድሮ እጅግ ምርጥ የድረ ገፅ አምደኛ የተባሉት አራሺ ሲርጋቺ የድረ ገፅ አምደኞችን በመወከል በአርአያነት ይጠቀሳሉ። ኢራን እንደ ሶርያ እና ምናልባትም እንደ ሩስያ መገናኛ ብዙኃንን ለራሳቸው ሥርዓት ማስከበሪያ ሊጠቀሙበት ከሚሞክሩ መንግሥታት መካከል ትቆጠራለች። እና በዚህ ዓይነት ጊዜ አምደኞች ፖሊቲካ መሪዎችን በኃላፊነት የመጠየቅና የማጋለጥ ሚና ስለሚጫወቱ አስፈላጊ ናቸው።

አያ ባኽ
አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 03.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14oB1
 • ቀን 03.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14oB1