የዳይመንድስ ሊግ በዙሪኽ | ስፖርት | DW | 28.08.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ስፖርት

የዳይመንድስ ሊግ በዙሪኽ

ካለፈው ግንቦት ወር ጀምሮ በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ማኅበር አዘጋጅነት በተለያዩ ከተሞች በመካሄድ ላይ ያለው የዳይመንድስ ሊግ ዛሬ ምሽት በስዊትዘርላንድ የዙሪኽ ከተማ በሚደረጉ ውድድሮች ይፈፀማል።

በነዚሁ ውድድሮች የዳይመንድስ ሊግ አጠቃላይ አሸናፊ ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው ከሚጠበቁት አትሌቶች መካከል በአምስትት ሺህ ሜትር የኔው አላምረው እና በሴቶች የ3,000 ሜትር መሰናክል ሕይወት አያሌው ይገኙባቸዋል። በ,ሴቶች 1,500 ለስዊድን የምትሮጠው አበባ አረጋዊ ለኔዘርላንድ በምትሮጠው ሰፋል ሀሰን መካከል ፣ እንዲሁም ፣ በ800 ሜትrር ኬንያዊው ዴቪድ ሩዲሻው ፣ መሀመድ አማን እና በቦትስዋናው ናጂል አሞስ መካከል ከፍተኛ ፉክክር ይጠበቃል።

ሃይማኖት ጥሩነህ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic