የዳዊት ይስሐቅ ጉዳይ እና የስዊድን ሕግ ባለሙያዎች ጥያቄ | አፍሪቃ | DW | 24.09.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የዳዊት ይስሐቅ ጉዳይ እና የስዊድን ሕግ ባለሙያዎች ጥያቄ

የስዊድን የሕግ ባለሞያዎች በስብዕና ላይ ወንጀል ፈፅመዋል ባሉዋቸው ከፍተኛ የኤርትራ ባለሥልጣናት ላይ ክስ እንዲመሠረት ያቀረቡበትን ጥያቄ የስዊድን ዓቃቤ ሕግ ውድቅ ካደረገባቸው በኋላ ይግባኝ ማመልከቻ አስገብተው መልሳቸውን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።

default

የሕግ ባለሙያዎቹ ጥያቄ በዋነኝነት ያተኮረው በኤርትራ በእስር የሚገኘው ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሐቅ ጉዳይ ላይ ነው። ዓቃቤ ሕግ ጉዳዩን ማጣጣሉን ድንበር የማይገድበው የጋዜጠኞች ድርጅት አሳፋሪ ብሎታል። ጋዜጠኛው ዳዊት ይፈታ ዘንድ ከሕግ ባለሙያዎቹ ጎን ድምፃቸውን የሚያሰሙ ወገኖችም የዳዊት ጉዳይ በአውሮጳ ሀገራትም ትኩረት ያገኝ ዘንድ የዳዊትን ስራ በተለያዩ ቋንቋዎች አስተርጉመው ለማውጣት እየሰሩ መሆናቸውን የስቶክሆልሙ ዘጋቢያችን ቴድሮስ ምህረቱ ገልጾልናል።

ቴድሮስ ምሕረቱ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic