የዳርፉር የሰላም ዉልና ትርጓሜዉ | ዓለም | DW | 25.02.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የዳርፉር የሰላም ዉልና ትርጓሜዉ

የሱዳን ማዕከላዊ መንግሥትና የዳርፉር ዋነኛ አማፂ ቡድን ከትናንት በስቲያ የተፈራረሙት የሰላም ዉል ሰባት አመት ያስቆጠረዉን የምዕራባዊ ሱዳን ግዛትን ግጭትና ጦርነት ለማስቆም እንደ አንድ ትልቅ እርምጃ እንደሚታይ የተለያዩ ወገኖች እየተናገሩ ነዉ።

default

ተፈራራሚዎቹ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፥ የአረብ ሊግ፥ የአፍሪቃ ሕብረትን የመሳሰሉት ድርጅቶችና ብሪታንያና ፈረንሳይን የመሳሰሉ ምዕራባዉን ሐገራት የሱዳን መንግሥትና የፍትሕና የእኩልነት ንቅናቄ (JEM በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ) የተሰኘዉ አማፂ ቡድን ዶሐ ቀጠር ዉስጥ ለተፈረሙት ዉል ድጋፋቸዉን እየገለጡ ነዉ።የሥምምነቱ ጥሩነት ተነግሮ ሳያበቃ ግን ዳርፉር ዉስጥ የመንግሥት ጦርና ሸማቂዎች መጋጨታቸዉ ተዘግቧል። ሥምምነቱንና ተቢራዊነቱን በተመለከተ ነጋሽ መሐመድ የአፍሪቃ ቀንድ የፖለቲካ ጉዳይ አዋቂ ሮላንድ ማርሻል በስልክ አነጋግሮ የሚከተለዉን ዘገባ አጠናቅሮታል። ነጋሽ መሀመድ ሂሩት መለሰ