የዳርፉር የሠላም ሥምምነት በቀጠር | ኢትዮጵያ | DW | 18.02.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የዳርፉር የሠላም ሥምምነት በቀጠር

ሥምምነቱን ብዙዎች እንደ መልካም እርምጃ ቢያዩትም አንዳድ የዳርፉር አማፂ ሐይላት ግን አልተቀበሉትም

default

ዶክተር ኻሊል ኢብራሒም (ከግራ)የጅም መሪ

የሱዳን ማዕከላዊ መንግሥት እና የፍትሕና የእኩልነት ንቅናቄ በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ (JEM) የተሰኘዉ የዳርፉር ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሥለሠላም ለመደራደር ትናንት ተስማምተዋል።ዶሐ-ቀጠር ዉስጥ ሥለ ሰላም ድርድር የተደረገዉ ሥምምነት ስድስት አመት የዘለቀዉን የዳርፉርን የርስበርስ ጦርነት በሰላም ለመፍታት እንደመጀመሪያዉ እርምጃ ታይቷል።ሥምምነቱን ብዙዎች እንደ መልካም እርምጃ ቢያዩትም አንዳድ የዳርፉር አማፂ ሐይላት ግን አልተቀበሉትም።ጂም ከዳርፉር አማፂያን ሁሉ ትልቁ ነዉ።የጂዳዉ ዘጋቢያችን ነብዩ ሲራክ ዝርዝሩን ልኮልናል።