የዲጂታል ልዩነት በኢትዮጵያ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 07.02.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የዲጂታል ልዩነት በኢትዮጵያ

የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በአፍሪካ ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት የሚታየው የዲጂታል ልዩነት (digital divide) ከፍ ያለ ነው፡፡ ኢትዮጵያም የዲጂታል ክፍተት በከፍተኛ ሁኔታ ከሚታይባቸው ሀገራት መካከል አንዷ እንደሆነች ጥናቶቹ ይጠቆማሉ፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 09:45

የዲጂታል ልዩነት በኢትዮጵያ

የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሀፊ ኮፊ አናን በኃላፊነታቸው ላይ በነበሩበት ወቅት አጠንክረው ከያዟቸው ጉዳዮች አንዱ “ሰዎች እንዳሻቸው የመገናኘት መብት አላቸው” የሚል ነበር፡፡ አናን “የመገናኘት ነጻነት እንደ ምግብ እና መጠለያ ሁሉ ለሰው ልጅ ጠቃሚ በመሆኑ ከመሰረታዊ የሰብዓዊ መብቶች መካከል እንደ አንዱ መቆጠር ይገባዋል” ሲሉ ሞግተዋል፡፡ ከዓመታት በኋላ ተመድ የሰዎች ግንኙነትን በማቅለል ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ያለውን የኢንተርኔት አገልግሎት እንደ መሰረታዊ የሰብዓዊ መብት ቆጥሮ እውቅና መስጠቱ ይፋ ተደርጓል፡፡ 

ለብዙዎች የህይወታቸው ዋነኛ አካል እስከመሆን የደረሰው ኢንተርኔት በተለያዩ ምክንያቶች እንደ ልብ ተደራሽ ያልሆነባቸው ሀገራት በርካታ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ በእንግሊዘኛ “digital divide” ተብሎ የሚጠራውን የዲጂታል አገልግሎት ልዩነት አስከትሏል፡፡ ለመሆኑ “digital divide” ምንድነው? አይስ አዲስ የተሰኘው የቴክኖሎጂ ድርጅት መስራች ማርቆስ ለማ ማብራሪያ አለው፡፡ 

የማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተምስ ባለሙያው እና ጉዳዩን አስመልክቶ የሚጽፈው በፍቃዱ ኃይሉ “የዲጂታል ልዩነት” (digital divide) ከኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (በምህጻሩ ICT) ተብሎ ከሚታወቀው ጋር የተያያዘ ነው ይላል፡፡ 

የኮምፒውተር እና ኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነየሩ ንጉሱ ሰለሞን ደግሞ የዲጂታል ልዩነቱን “ከተደራሽነት፣ ከእኩልነት እና ከከተማ መስፋፋት አንጻር” ይመለከተዋል፡፡ ሀሳቡን ለማብራራት ምሳሌ በማቅረብ ይጀምራል፡፡ የአይስ አዲሱ ማርቆስ በኢትዮጵያ ያለውን የዲጂታል ልዩነት በቁጥር አስደግፎ ያስረዳል፡፡  

በኢትዮጵያ ያለውን የዲጂታል ልዩነት በሁለት መንገድ መመልከት ይገባል ይላል በፍቃዱ፡፡ አንደኛው ኢትዮጵያ ከመላው ዓለም ጋር ባላት ንጽጽር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በኢትዮጵያውያን የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ተጠቃሚዎች በሆኑ እና ባልሁኑ ዜጎች መካከል ያለው ልዩነት እንደሆነ ያብራራል፡፡  በዲጂታል ልዩነት ውስጥ የሚኖር ማህብረሰብ ጉዳት እንደሚደርስበት የሚያጠራጥር አይደለም ባይ ነው የኮምፒውተር ኢንጂነሩ ንጉሱ፡፡ ንጉሱ የዲጂታል ልዩነቱን ለማስተካከል ሁሉም ኃላፊነት አለበት ብሎ ያምናል፡፡ ማርቆስ በበኩሉ ልዩነቱን ለማጥበብ ይረዳሉ የሚላቸውን መፍትሔዎች ይዘረዝራል፡፡   

እንደ ማርቆስ ሁሉ ለችግሩ የፖሊሲ መፍትሄ ያስፈልገዋል ብሎ የሚያምነው ንጉሱ ሌሎች የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም ጠቁሟል፡፡ ሙሉ ዝግጅቱን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።  

ተስፋለም ወልደየስ 

ሂሩት መለሰ 
 

Audios and videos on the topic