የዲላው ጥቃት ያስከተለው ጉዳት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 12.10.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የዲላው ጥቃት ያስከተለው ጉዳት

ጥቃት አድራሾቹ በብዛት በመውጣት አዛውንት ህጻን ሴት ሳይለዩ ሕይወት ማጥፋታቸውን ፣ ሰዎችን ማቁሰላቸውን እና ቤቶችን እና የተለያዩ ንብረቶችን ማቃጠላቸው ተገልጿል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 05:01
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
05:01 ደቂቃ

የዲላው ጥቃት ያስከተለው ጉዳት

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በደቡብ ክልል በሚገኘው በዲላ እና በአካባቢው ከተሞች በደረሰው ጥቃት ከተፈናቀሉት እና ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች መካከል የአካባቢው ተወላጆችም እንደሚገኙበት ተነገረ። ለንደን ነዋሪ የሆኑ አንድ የአካባቢው ተወላጅ ጥቃት አድራሾቹ በብዛት በመውጣት አዛውንት ህጻን ሴት ሳይለዩ ህይወት ማጥፋታቸውን ፣ ሰዎችን ማቁሰላቸውን እና ቤቶችን እና የተለያዩ ንብረቶችን ማቃጠላቸውን በስልክ ከቤተሰቦቻቸው አባላት እንደሰሙ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። ያነጋገረቻቸው የለንደንዋ ወኪላችን ሀና ደምሴ ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅታለች።

ሀና ደምሴ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic