የዱር እንስሳ ንግድን የተመለከተዉ ከፍተኛ ጉባዔ  | ዓለም | DW | 29.09.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የዱር እንስሳ ንግድን የተመለከተዉ ከፍተኛ ጉባዔ 

የዱር እንስሳ ንግድን የተመለከተዉ ከፍተኛ ጉባዔ 

የአፍሪቃ ዝሆኖች ጥርስ እና የአዉራሪስ ቀንድ ሽያጭ ዝዉዉር ኢትዮጵያን ጨምሮ የምሥራቅ፤ መካከለኛና የደቡባዊ አፍሪቃ ሃገራትን እያወዛገበ ነዉ። በደቡብ እና ምሥራቅ እስያ ገበያዉ የደራዉ የዝሆን ጥርስ ለሃብት መገለጫ እና ለጥበብ ሥራዎች ይዉላል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:44
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
02:44 ደቂቃ

የዱር እንስሳት ተመልካች ጉባዔ 

እንዲሁም  የአዉራሪስ ቀንድ ተፈጭቶ በቬትናም እና ቻይና ለባህላዊ መድሐኒትነት በከፍተኛ ደረጃ ጥቅም ላይ ይዉላል። በደቡብ አፍሪቃ በመካሄድ ላይ በሚገኘዉ ዝርያቸዉ ለአደጋ የተጋለጡ የዱር እንስሳትና እጽዋት ዓለም አቀፍ ጉባዔ፤ የዝሆንና መሰል እንስሳት አደን እንዲታገድ፤ አንዳንዶቹም ጠንካራ ቅጣት እንዲጣል በመጠየቅ እየተከራከሩ ነዉ። በዚህ ጉባኤ ላይም ከ2 ሺህ የሚበልጡ ከ180 ሃገራት የተዉጣጡት ተሰብሳቢዎች መገኘታቸዉን የጀርመን የዜና ወኪል DPA አመልክቷል። ደቡብ አፍሪቃ የሚገኘዉ ዘጋቢያችን ዝርዝሩን ልኮልናል። 


መላኩ አየለ


አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic