የደ/ሱዳን ተቀናቃኞች የፊት ለፊት ንግግር | አፍሪቃ | DW | 09.05.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የደ/ሱዳን ተቀናቃኞች የፊት ለፊት ንግግር

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች ለዛሬ እንደተቀጠረዉ ለፊት ለፊቱ ዉይይት አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ዛሬ ከቀትር በፊት መድረሳቸዉ ሲገለፅ፤ የቀድሞ ምክትላቸዉና የአማፅያኑ መሪ ሪክ ማቻር ደግሞ ትናንት ማምሻዉን ነዉ አዲስ አበባ ገብተዉ ያደሩት።

የጀርመን የዜና ወኪል ከአዲስ አበባ እንደዘገበዉ ማቻር በመንግስት ታስረዉ ከቆዩትና ከተለቀቁት የቀድሞ ባለስልጣናት ጋ ተገናኝተዉ ተነጋግረዋል። ከወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝም ጋ እንዲሁ መነጋገራቸዉ ተገልጿል። አሁን መሳሪያ የተማዘዙትን ሁለቱን የጁባ ከፍተኛ ፖለቲከኞች ከያሉበት ለድርድር እንዲመጡ ኢትዮጵያ ብትጋብዝም በማግባባት እንዲመጡ የተመድ ዋና ፀሐፊ ባን ጊ ሙንና የአሜሪካዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ከፍተኛ ሚና መጫወታቸዉን ዘገባዉ ጨምሮ ገልጿል። እስካሁን ሁለቱ ተቀናቃኞች መገናኘታቸዉን የሚገልፁ ዘገባዎች ባይወጡም ዘጋቢያችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደገለጸልን ተገናኝተዉ ሳይወያዩ አልቀሩም። ስለዉይይቱ መግለጫ በመጠባበቅ ላይ የሚገኘዉን የአዲስ አበባ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስን ስለሁኔታዉ በአጭቱ አነጋግሬዋለሁ፤

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic