የደንጉ ትኩሳት በሽታ ሥጋት በድሬዳዋ | ኢትዮጵያ | DW | 05.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የደንጉ ትኩሳት በሽታ ሥጋት በድሬዳዋ

ሰሞኑን የድሬደዋ ከተማ ህዝብ የወረርሽኝ በሽታ ሳይገባ አይቀርም በሚል ሥጋት ላይ ይገኛል።በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለታየው በሽታ ምንነት እና ክትትል…

ቁጥራቸው ከወትሮው የተለየ ህሙማን በአሁን ሰዓት በድሬደዋ ከተማ መመዝገባቸው ብዙዎችን ስጋት ላይ ጥሏል። የጥቅምትና ህዳር ወር የወባ በሽታ በሰፊው የሚስተዋልበት ጊዜ ቢሆንም ምርመራው ከተደረገላቸው ውስጥ 300 የሚሆኑት ብቻ ናቸው በወባ በሽታ መያዛቸው የተረጋገጠው። በወባ በሽታ ከተያዙ ሰዎች ሌላ ወደ ሁለት ሺ የሚደርሱ ሰዎች በደማቸው ውስጥ የወባ በሽታ አለመገኘቱን የድሬዳዋአስተዳደርጤናቢሮኃላፊ- አቶካሣሁንኃ/ጊዮርጊስ ገልጸዋል።

ለበለጠ ምርመራ ወደ አዲስ አበባ የጤናና ሥነ-ምግብ ምርምር ኢንስቲቱዩት የተላከው ምርመራ እንደሚያሳየው ግን የደንጉ ትኩሳት መሆኑ ሊረጋገጥ ችሏል። በሽታው ከወባ በሽታ ጋ ተመሳሳይ የህመም ምልዕክት እንዳለውም አቶ ካሳሁን ለዶይቸ ቬለ አስረድተዋል።

ትኩሳት ፣ ራስ ምታት እና ነስር የዚህ የደንጉ ትኩሳት ዓይነተኛ ምልክቶች ሲሆኑ እስካሁን በበሽታው የሞተ ሰው እንደሌለ ነው አቶ ካሳሁን የገለፁልን።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic