የደንጉ ትኩሳት መከላከያ ግኝትና ችግሩ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 24.12.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የደንጉ ትኩሳት መከላከያ ግኝትና ችግሩ

የተለያዩ አራት ዓይነት የደንጉ ትኩሳት በሽታ አምጭ ተሐዋሲዎችን ለመከላከል የተገኘዉ መድሐኒት በሽታዉን ለማምከን አቅም እንዳለዉ ቢገለፅም፤ በክትባት መልክ ለተጠቃሚ ለማድረስ የሚደረገዉ ጥረት ግን ብዙ መሰናክል ተደቅኖበታል።

የበሽታ መከላከያ ጉዳይ ምሁሩ ቤርንድሃርድ ፍላይሸር እንደሚሉት ችግሩ መድሐኒት ማግኘት ሳይሆን ማምረቱ ላይ ነዉ።

እንግሊዝ የህክምና ባለሞያዎች አራት ዓይነት የደንጉ ትኩሳት በሽታን የሚያስከትሉ ተሐዋሲዎችን የሚያጠቁ መድሐኒትን አግኝተዋል። የዚህን በሽታ መከላከያ መድሐኒት ማግኘት ምን ያህል ጠቀሜታን ይሰጥ ይሆን? እንደ ጀርመናዊዉ የሰዉነት ሕክምና ባለሞያና ተመራማሪ እንደ ዶክተር ቤርንድሃርድ ፍላይሸር እንደሚሉት በዚህ አይነቶቹ ተሐዋሲዎች የተያዘ ሰዉ በሰዉነት ዉስጥ ምንም ዓይነት የበሽታ መከላከያ ህዋስ አይኖረዉም ሲሉ ይገልፃሉ።

Prof. Dr. Bernhard Fleischer

ጀርመናዊዉ የሰዉነት ሕክምና ባለሞያና ተመራማሪ እንደ ዶክተር ቤርንድሃርድ ፍላይሸር


« አንድ ሰዉ በነዚህ አራት የደንጉ ትኩሳትን አምጭ ተሐዋሲዎች ከተያዘ፤ ሰዉነቱ ከሌሎች የበሽታ ተሐዋሲዎች የመከላከል አቅም አይኖረዉም። በዚህም ምክንያት አራት ጊዜ በደንጉ የትኩሳት በሽታ ተጠቂ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ አንድ ግለሰብ በዚህ በሽታ ለሁለተኛ ጊዜ ሲያዝ ለመጀመርያ ጊዜ ሲያዝ ከነበረዉ ሕመም እጅግ ከባድ ሕመም ሁሉ ሊገጥመዉ ይችላል። በዚህም ነዉ፤ የዚህን አራት አይነት በሽታ አምጭ ተሐዋሲዎችን ለመከላከል አንድ የመከላከያ ክትባት ማግኘት ግድ ያለዉ»
የደንጉ ትኩሳት በሽታ ለሁለተኛ ጊዜ የተያዘ ሰዉ ህመሙ ከመጀመርያዉ ጊዜ እጅግ ሊጠናበት እንደሚችል የሕክምና ባለሞያዉ ዶክተር ቤርንድሃርድ ፍላይሸር ገልፀዋል።
«ለመጀመርያ ጊዜ በዚህ ተሐዋሲ የተያዘ ሰዉ ሰዉነት የበሽታ ተከላካይ ህዋስን መከላከል የሚችል ህዋስ መሥራት ስለማይችል ነዉ። በዚህም በሰዉነት ዉስጥ ይበልጥ በሽታዉ የመሰራጨት እቅሙ ይጨምራል። ግን ይህ ጉዳይ መንስኤ የመሆኑ ጉዳይ አሁንም መልስ ያላገኘ አጠያያቂ ጉዳይ ነዉ። በተጨማሪ በሰዉነት ዉስጥ የደንጉ ትኩሳት ለምን ያህል ጊዜ አዘዉትሮ እንደሚመጣ ግልፅም አይደለም። ግን ዋናና የተረጋገጠዉ ነገር፤ በደንጉ የትኩሳት ተሐዋሲ ተይዘን ከነበር፤ ለሁለተኛ በዚህ በሽታ እንዳንያዝ ሰዉነታችን መከላከያን መሥራት አይችልም»
የምርምሩ ግብ አራቱንም የደንጉ ትኩሳት አምጭ ተሐዋሲዎች ማምከን የሚችል መከላከያ መድሃኒት ማግኘት ነዉ። ይህን የመከላከያ ክትባት ለመሥራት ምን ያህል ጊዜን ይፈጅ ይሆን? « ምርምሩ ገና በመሰረታዊ ጥናት ደረጃ ላይ ነዉ የሚገኘዉ። በምርምሩ ሥራ የመጀመርያ ደረጃ በአራቱም ተሐዋሲዎች አንድ የጋራ የሆነ ቦታን ማግኘት ነዉ። ከዝያም አራቱንም ተሐዋሲዎች ማጥፋት እንዲያስችል በዚህ ቦታ ላይ መድሐኒቱን ማድረግ ነዉ»
ስለዚህም እንደ ጥናቱ ግኝት ይላሉ ዶክተር ቤርንድሃርድ ፍላይሸር እዚህ ልዩ ቦታ ላይ የሚገኘዉን አራት ተሐዋሲዎች ለማጥፋት አንድ የመከላከያ ክትባት መሰራት ይኖርበታል። እዚህ ላይ ችግሩ፤ ሰዉነት ዉስጥ የሚገኘዉ የበሽታ ተከላካይ ህዋስ ሰዉነታችን ቀላል ህመም ላይ በሚወድቅበት ግዜ ለግዜዉ መከላከያ የሚሆን ህዋስ ይገነባና ያቆማል። ይህ የበሽታ ተከላካይ ህዋስ በሰዉነታችን ዉስጥ ለጊዚዉ አልያም ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነዉ የመከላከል ኃይል የሚኖረዉ። በመሆኑም በአንዱ የደንጉ ትኩሳት በሽታ አምጭ ተሐዋሲ የታመመ ሰዉ ከሌሎች ተሐዋሲ አይነቶች የተጠበቀ አይደለም። በዚህ ረገድ ይህን ተሐዋሲ እንዳይጠፋ ያጠናከረዉን ህዋስ ለመግደል አንድ አዲስ መከላከያ ማስፈለጉ ተመልክቶአል። እነዚህ በሽታ ተከላካይ ህዋሳት በሰዉነታችን ዉስጥ እርስ በርሳቸዉ በመራባት መጠናቸዉን በመጨመር ከሌሎች የደንጉ ትኩሳት በሽታ አምጭ ተሐዋሲ ጋር መዋጋት እንዲችል ነዉ።
ግን ይህን ለማግኘት ገና ከባድ ጉዞን እንደሚጠብቅ ነዉ የተመለከተዉ። ምንም እንኳ ይህን መፍትሄ ለማግኘት ረጅም ጎዞን ማስፈለጉ ታወቀ እንጂ ገና መድሐኒቱ የተገኘ አለመሆኑም ነዉ የተመለከተዉ።


«ልክ ነዉ፤ ግን የተሳካ ሆንዋል። እዚህ ላይ የሚያስደንቀዉ ነገር ይህ ተሐዋሲ የሚመጣዉ በቢምቢ መሆኑ ነዉ። ተሐዋሲዉ በመጀመርያ በቢምቢ አካል ዉስጥ ይራባል፤ ቢንቢዋ ደግሞ ወደ ሰዉ ታስተላልፋለች። ከዝያ ሰዉነት ዉስጥ ተራብቶ የሰዉነት ህዋሳትን ይወራል ። ይህ አዲሱ መድሐኒት ከሁሉም አይነት የደንጉ ትኩሳት በስታ አምጭ ተሐዋሲ መከላከል ይችላል»
ይህ የበሽታ መከላከያ በቢምቢ በኩል ወደ አካላችን የገባዉን ተሐዋሲንም ሆነ በአካላችን ዉስጥ የተራባ ተሐዋሲን የመከላከል አቅም አለዉ። በዚህም ነገሩ እጅግ አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል። ከዚህ የምንማረዉ አንድ ነገር፤ ሰዉነታችን የተሐዋሲ መከላከያ በነጭ የደም ሴሎች አማካኝነት ይህን አይነት መከላከያ እንዲያመነጩ በማድረግ ጥሩ የመከላከያ ዘዴን መፍጠር ነዉ።
ችግሩ ጎልቶ የሚታየን ግን ጉዳዩን በጥልቅ ስናየዉ ነዉ። ይህ የበሽታ መከላከያ ህዋስ የተሐዋሲዉን የተወሰነ ክፍል እንዲያጠፋ ሆኖ መሰራት ይኖርበታል። አራቱም ተሐዋሲዎች በአንድ ቦታ በቀላሉ ማግኘት አይቻልም። የብዙ ፕሮቲን ንዑስ ክፍል ጥምር በመሆኑ ነዉ። ስለዚህ አንድ ክትባት ይህንን አይነቱን ክትባት መከላከያ መስራት መቻሉን አላወቅንም ሲሉ ዶክተር ቤርንድሃርድ ፍላይሸር ገልፀዋል።
«Chimerivax » «ቼሜ ሪቫክስ» የተሰኘ ሌላ ለክትባት የሚሆን መድሃኒት «ሳኖፊ ፓስቶር» በተሰኘዉ የክትባት አምራች ድርጅት ተሰርቶአል። ይህ ክትባት አራቱም አይነት የደንጉ ትኩሳት በሽታ አምጭ ተሐዋሲዎችን ማጥፋት እንደሚችል ይነገራል። አዲሱ የምርምር ዉጤት ታድያ ከዚህ መድሐኒት የሚለየዉ ምን ይሆን?
ድምፅ ዶክተር ቤርንድሃርድ ፍላይሸር
« አዲሱ የክትባት ምርምር ግኝት ዉጤት አራቱንም አይነት የበሽታ አምጭ ተሐዋሲ ለመከላከል የሚያስችል አቅም ያለዉና መድሐኒቱን ከአንድ የፕሮቲን ንዑስ ክፍል ብቻ ማምረት መቻሉ ነዉ። ይህ ደግሞ እጅግ አመቺን ሁኔታን የሚፈጥር ነዉ። ችግሩ ግን ይህንን የፕሮቲን ንዑስ ክፍል ማምረት ነዉ ። ምክንያቱም ይህ የፕሮቲን ንዑስ ክፍል አንድ ብቻ ሳይሆን ከሁለት የፕሮቲን ንዑስ ክፍሎች በተወሰነ መጠን ተጣምሮ የሚመረት ነዉ»
ሌላዉ አማራጭ ደግሞ አራቱንም አይነት የደንጉ ትኩሳት በሽታ መከላከል የሚችል አንድ የክትባት መድሐኒት ማምረት ነዉ። «ቼሜ ሪቫክስ» የሚባለዉ የክትባት መድሐኒት አራቱንም አይነት የደንጉ ትኩሳት አምጭ ተሐዋሲዎችን ዉስጡ የያዘ ሲሆን ፤ ይህ አዲስ የሚሰራዉ የመከላከያ ክትባት ቴክኖሎጂ የአራቱንም ተሐዋሲያን የያዘ አንድ የፕሮቲን ንዑስ ክፍል ብቻ ነዉ ያለዉ።


ይህ አዲስ የመከላከያ ክትባት ታይላንድ ዉስጥ እየተሞከረበት ነዉ። በሌላ በኩል ሰፊ ጥናቶች እየተካሄደበትምና ከፍተኛ በሽታዉን የመከላከል አቅም እንዳለዊ ምልክቶችን እያሳየ ነዉ። ግን ፍጹም ነዉ ማለትም አይቻልም። እስካሁን ይህን ክትባት ከተሰጣቸዉ ህጻናቶች መካከል ሲሶ ያህሉ ከዚህ በሽታ ተጠብቀዉ ይገኛሉ። ስለዚህ ክትባቱ መቶ በመቶ ይከላከላል ብለን መግለፅ አይቻልም ሲሉ ዶክተር ቤርንድሃርድ ፍላይሸር ተናግረዋል።
ለሁለተኛ ጊዜ በደንጉ ትኩሳት ተሐዋሲ የሚታመም ሰዉ በዚህ በአዲሱ ክትባት መድሐኒት ረዳትነት ብዙ ስቃይ አይደርስበትም ማለት ነዉ?
« ምኞታችን ይህ ነበር ግን ገና ብዙ ጥናቶችን ማካሄድ ይኖርብናል። » የደንጉ ትኩሳት በሽታ ዓይነተኛ ምልክቶች ፤ ጉንፋን አይነት ልክት ትኩሳት ፣ ራስ ምታት እና ነስር ዓይነተኛ ምልክቶች ናቸዉ። ይህ ተላላፊ በሽታ ደግሞ በዋነኛነት በቢምቢ ወደ ሰዎች እንደሚዛመትም ተመልክቶአል። ስለደንጉ ትኩሳት በሽታ መከላከያ አዲስ መድሐኒት ግኝትና መከላከያ ክትባት ለመስራት ስለገጠመዉ መሰናክልr ቃለ ምልልስ የሰጡን በጀርመን ሃንቡርግ የሞቃታማ ሃገሮች የሕክምና መድሃኒት ምርምር ተቋም ተጠሪ ፕሮፊሰር በርሃርድ ፍላይሸር ነበሩ።

ፋቢያን ሽሚድ / አዜብ ታደሰ


ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic