የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ | ኢትዮጵያ | DW | 02.08.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ

ደቡብ ክልል ለበርካታ ዓመታት በመጓተት ላይ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች በቶሎ እንዲጠናቀቁ የክልሉ ምክር ቤት አባላት ጠየቁ። ምክር ቤቱ ስድስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን ጉባኤውን ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ጀምሯል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:47

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ

ደቡብ ክልል ለበርካታ ዓመታት በመጓተት ላይ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች በቶሎ እንዲጠናቀቁ የክልሉ ምክር ቤት አባላት ጠየቁ። ምክር ቤቱ ስድስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን ጉባኤውን ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ጀምሯል። ውሎውን ሲያጠናቅቅም የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለ2014 በጀት ዓመት የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ማስፈጸሚያ 49 ቢሊየን ፣ 43 ሚሊየን፣ 502ሺ፣ 423 ብር ጥቅል በጀት አጽድቋል። በምክር ቤቱ ከፀደቀው ጠቅላላ በጀቱ ውስጥ 34 ነጥብ 2 ቢሊየን የሚሆነው ከፌደራል መንግሥት ድጎማና ከውጭ ርዳታ የሚገኝ ሲሆን 14 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የሚሆነው ደግሞ ከክልሉ ልዩ ልዩ ገቢዎች የሚሰበሰብ እንደሚሆን ጉባኤውን በመከታተል ላይ የሚገኘው የሀዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ ተጨማሪ ዘገባ ያመለክታል ። ጉባኤው በዛሬው ውሎው በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በቀረበው የ2014 ዓም ረቂቅ የሥራ ዕቅድ ላይ ተወያይቷል።

 ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች