የደቡብ አፍሪቃ የነጻነት በዓል እና ተቃውሞ | አፍሪቃ | DW | 27.04.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የደቡብ አፍሪቃ የነጻነት በዓል እና ተቃውሞ

በዓሉ በተለይ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጄኮብ ዙማ በተገኙበት ሲከበር በመንግሥቱ መቀመጫ በፕሬቶሪያ ደግሞ ተቃውሞ ተካሂዷል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:13

የደቡብ አፍሪቃ የነጻነት በዓል እና ተቃውሞ

 
ደቡብ አፍሪቃ ከጥቂት ውሁዳን ነጮች አገዛዝ ነጻ የወጣችበትን 23 ተኛ ዓመት ዛሬ አክብራለች። በዓሉ በተለይ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጄኮብ ዙማ በተገኙበት በክዋዙሉ ናታል ክፍለ ግዛት በማንጉዞ ከተማ በተለያየ ስነ ስርዓት ሲከበር በመንግሥቱ መቀመጫ በፕሬቶሪያ ደግሞ ተቃውሞ ተካሂዷል ። በፕሪቶሪያ በተካሄደ ሰልፍ ላይ የተካፈሉ ተቃዋሚዎች ፕሬዝዳንት ጄኮብ ዙማ ከሥልጣን እንዲወርዱ ጠይቀዋል። ዝርዝሩን የጆሀንስበርጉ ዘጋቢያችን መላኩ አየለ ልኮልናል 
መላኩ አየለ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ 

Audios and videos on the topic